Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ2018 በጀት ዓመት ለዲስትሪክቱ የመንገድ ጥገናና ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው የማጠናከሪያ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ኢመስ/ሻሽ/088/2018

 

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት 2018 በጀት ዓመት ለዲስትሪክቱ የመንገድ ጥገናና ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው የማጠናከሪያ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠብቅባቸዋል።

1.     ተጫራቾች 2018 . የታደሰ ንግድ ፍቃድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርቲፍኬት እና የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

2.     ተጫራቾች 2017 በጀት ዓመት ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።

3.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።

4.     ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በእለቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5.     ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው 16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኃላ 800 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከቀኑ 830 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል። በእለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

6.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000002579859 ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ዕቃ ግዥ///አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።

7.     በጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።

8.     ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 211 4616 መጠቀም ይችላሉ።

9.     /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሽመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት

Save Tender