Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
  • Address አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-56-98-69
  • Websitehttps://press.et/
  • Deadline15 Jun 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100.00
  • opening date2026-06-15 10:30:00
  • Categories Vehicle

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ለከፍተኛ አመራሮች የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡-ኢፕድ 023/2018

 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 2018 በጀት ዓመት ለከፍተኛ አመራሮች የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም፡ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።

1.       በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግሥት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

2.       ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብርበመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል መሆኑና ግዥውን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ 16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው በአቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

3.       ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብርበባንክ በተረጋገጠ ../ቢድ ቦንድ ማስያዝ አለባቸው።

4.       ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምሪያ ከረፋዱ 400 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 430 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 1 ፎቅ በአቅርቦት መምሪያ ይከፈታል። ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ባለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

5.       /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 011 156 9869

ኢሜይል procurement@press.et

አድራሻ  አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት

 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

Save Tender