Tender Detail

Tender Details


ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንች ሸኮ እና በምዕራብ ኦሞ ዞን በአምስት ወረዳዎች በሚገኙ 15 (አስራ አምስት) 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶችና 4 (አራት) ጤና ተቋማት፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሃዲያ ዞን  በምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳ በሚገኙ 4 (አራት) 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶችና 2 (ሁለት) ጤና ተቋማት፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በሀመር እና በበና ጸማይ ወረዳዎች በሚገኙ 6 (ስድስት) 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶችና 4 (አራት) ጤና ተቋማት እንዲሁም በሲዳማ ክልል በሃቤላ ወረዳ በሃቤላ ሊንዳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በድምሩ በ 26 ት/ቤቶች እና በ 10 ጤና ተቋማት  የዝናብ ዉሃ መሰብሰቢያና የፊት መታጠቢያ ለመገንባት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የግንባታ ማህበራትን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንች ሸኮ እና በምዕራብ ኦሞ ዞን በአምስት ወረዳዎች በሚገኙ 15 (አስራ አምስት) 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶችና 4 (አራት) ጤና ተቋማት፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሃዲያ ዞን  በምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳ በሚገኙ 4 (አራት) 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶችና 2 (ሁለት) ጤና ተቋማት፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በሀመር እና በበና ጸማይ ወረዳዎች በሚገኙ 6 (ስድስት) 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶችና 4 (አራት) ጤና ተቋማት እንዲሁም በሲዳማ ክልል በሃቤላ ወረዳ በሃቤላ ሊንዳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በድምሩ በ 26 ት/ቤቶች እና በ 10 ጤና ተቋማት  የዝናብ ዉሃ መሰብሰቢያና የፊት መታጠቢያ ለመገንባት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የግንባታ ማህበራትን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡   በዚህም መሰረት፡-

  1. ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸዉን እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት  ያላቸዉ፣
  2. የዉሃ ስራ ደረጃ 8 ወይም 9 ያላቸዉ፣ ወይም የግንባታ ፈቃድ ደረጃ 8  ያላቸዉ፣
  3. ህጋዊ የምዝገባ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ከዞን ዉሃ ወይም ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ወይም ከዚህ በፊት ከሰሩበት ዞን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ማህበራቱ በጨረታ ሰነዱ ዉስጥ የተዘረዘሩትን የግንባታ ቁሳቁስ በግዥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  6. ተጫራቾች የጨረታዉን ዶክመንት ከኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል የፕሮጀክቱ ማሰተባበሪያ ቢሮ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሃዲያ ዞን የኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የፕሮጀክቱ ማሰተባበሪያ ቢሮ፣ በሲዳማ ክልል ሃዋሳ ከተማ የኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የፕሮጀክቱ ማሰተባበሪያ ቢሮ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን የፕሮጀክቱ ማሰተባበሪያ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 15/2018 ዓ/ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ብር 00 በኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የህብረት ባንክ አካዉንት ቁጥር 1131810577203010 በማስገባትና ደረሰኝ በማቅረብ መዉሰድ ይችላሉ፣
  7. ተጫራቾች ኦርጂናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ዶክመንቶችን እና የግንባታ ቁሳቁስ እና የጉልበት ጥቅል ዋጋ  በወሰዱት የጨረታ ሠነድ ላይ ሞልተዉ ኦሪጂናል፣ ኮፒ 1 አና ኮፒ 2 ብለዉ በመጻፍና በአንድ ኢንቨሎፕ ዉስጥ በማድረግ በጥንቃቄ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ሰኔ 15/2018  ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በወሰዱበት የኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ  የፕሮጀክቱ ማሰተባበሪያ ቢሮ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፣`
  8. አንድ ማህበር ከ7 (ሰባት) የግንባታ ቦታዎች በላይ መወዳደር አይችልም፣ ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸዉን ት/ቤቶች እና ጤና ተቋማት  ስም በፖስታዉ ላይ በግልጽ መጥቀስ አለባቸዉ፣ እንዲሁም ተጫራቾች የሚያቀርቡት የግንባታ ቁሳቁስ እና የጉልበት ዝርዝር ዋጋ የወቅቱን ገበያ ግምት ዉስጥ ያስገባ መሆን አለበት፣
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት የ 500 (አምስት ሽህ) ብር CPO (ለአንድ ት/ቤት) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  10. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፣
  11. ከዚህ በፊት በአፈጻጸማቸዉ ማስጠንቀቂያ የተጻፈባቸዉ ማህበራት መወዳደር አይችሉም፡፡

ማሳሰቢያ፡ የጨረታ ሰነዱን ለመዉሰድ ሲመጡ የማህበሩን የታደሰ ፈቃድ ኮፒ ይዘዉ  ይቅረቡ፣ የት/ቤቶቹን መረጃ ከአባሪዉ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡ በ 0116 62 09 96 ወይም ለሚዛን በ09 17 25 94 24/ 09 11 24 95 53  ፣ ለምዕራብ ባዳዋቾ በ09 17 82 25 78 ፣ለደቡብ ኦሞ በ09 79 81 04 89/ 09 17 82 25 78 ለሲዳማ በ09 73 99 56 21 ይደዉሉ፡፡

Save Tender