Tender Detail

Tender Details


የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለድሬዳዋ ፌዴራል ፖሊስ ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዝርዝራቸው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘ የስራ ዝርዝር (Specification) መሰረት የ submersible & Water Pump አቅርቦትና ገጠማ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCE/SF/79/2026

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለድሬዳዋ ፌዴራል ፖሊስ ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዝርዝራቸው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘ የስራ ዝርዝር (Specification) መሰረት የ submersible & Water Pump አቅርቦትና ገጠማ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

 

የስራ ዝርዝር

 

የጨረታ ቁጥር

 

የጨረታ መዝጊያ ቀን

 

የጨረታ መክፈቻ ቀን

 

1

 

Supply install, test & Commission Submersible & Water Pump

 

DCE/SF/79/

2026

 

24/10/2018 ዓ.ም ከቀኑ 08፡30

 

24/10/2018 ዓ.ም ከቀኑ 08:45

 

 

ስለሆነም፡-

1.    ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፣ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2.    ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንከ በተረጋገጠ CPO ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3.    3.ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔስፍኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል።

4.    ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ዝቅ ብሎ የቀድሞ መ.ኮ.ድ ግቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መስሪያ ቤት የግዥ እና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ መግዛት ይችላሉ።

5.    ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሠነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 08፡30 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6.    ጨረታው ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 08፡45 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል።

7.    አንድ ተጫራች ለአንድ ዕቃ መወዳደር የሚችለው በአንድ ዓይነት ሞዴል/ብራንድ/ ብቻ ነው በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።

8.    ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ቃሊቲ ቶታል ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ገቢ የቀጥታ ስልክ ቁጥር ቁጥር 011 440-3434/33

H&P 011 442-2270/71/72 www.dce-et.com (http://www.dce-et.com/) /Email: - info@dce-et.com 

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

Save Tender