Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address የሀዲያ ዞን ፣ኢትዮጲያ, Phone: 046-555-2337
  • Website
  • Deadline24 Jun 2026, 11:00 AM
  • magazineAdiss zemen
  • Bid Document Price
  • opening date2026-06-24 11:30:00
  • Categories Vehicle

የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች(መኪናዎች፡ ትራከተሮች ፣ ተጎታች ጋሪ ፡ ሞተር ሳይክሎች እና ብስክሌት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ



የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች(መኪናዎች፡ ትራከተሮች ተጎታች ጋሪ ሞተር ሳይክሎች እና ብስክሌት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡-
ሎት -1 መኪናዎች
ሎት-2 ትራከተሮዎች
ሎት-4 ሞተር ሳይክሎች
ሉት-5 ብስክሌት
1.
ተሸከርካሪዎቹ የሚገኙበት አድራሻ ሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ እና ሀዲያ ዞን ጤና መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
2.
በተሽከርካሪዎች ጨረታ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል፡፡
3.
ተጫራቾች ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም እና የተጫራቾች መመሪያ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 10 /አስር/ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በተናጠል፡- ሎት- መኪና ብር 400.00/አራት መቶ ብር/ ሎት-2 ትራክተር ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ ሎት-3 ተጎታች ጋሪ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ ሎት 4 ሞተር ሳይክል ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ እና ሎት- 5 ብስከሌት ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመከፈል ከሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 17 በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

4.
ተጫራቾች የሚወዳደሩትን ተሽከርካሪ/ዎች በሎት በተናጠል ወይም በድምር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመነሻ ዋጋ 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡

5.
የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ መሙያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታ አንድ ዋና/Original/ እና ቅጂ/Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በፖስታ ታሽጎና እንደገና ሁለቱም በአንድ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በሰም በማሸግ ቢሮ ቁጥር 17 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

6.
ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በእሃዝና በፊደል በመጻፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፈት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለባቸው ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም፡፡

7.
ተጫራቾች ለመግዛት የፈለጉትን ተሸከርካሪ/ዎች የጨረታ ዋስትና ካስያዙት ተሽከርካሪ/ዎች ውጪ መወዳደር አይቻልም፡፡

8.
ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ከአንድ በላይ ተሽከርካሪ መጫረት ይችላሉ፡፡

9.
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው/አስራ አንድ/ ቀን ከረፋዱ 500 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ 530 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

10.
ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሸከርካሪዎች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ በተገለጸ 1/አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው ሆኖም በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ገዢው ካላነሳ ለሚደርሰው ለማንኛውም ችግር ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም።

11.
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ከመንግሥት የሚፈለግ ግብርና ቀረጥ በሻጩ የሚሸፈን ይሆናል።

12.
አሸናፊው ተጫራች የተሽከርካሪ ስም ማዘዋወሪያ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች በሙሉ በአሸናፊው ይሸፈናል።

13.
ተጫራቾች የመነሻ ዋጋ እና የዋጋ ማቅረቢያ የጨረታ ሰነድ አካል ሲሆን ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘ ነው፡፡:00

14.
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ ሙበቱ የተጠበቀ ነው:: ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046-555-2337/2316 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

Save Tender