መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር ያገለገሉ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ሠነድ ያላቸውና የሌላቸው 18 ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 126
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር ያገለገሉ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ሠነድ ያላቸውና የሌላቸው 18 ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተሽከርካሪዎቹን ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 03 (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከፀበል መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን) ፊት ለፊት በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 14 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከጧቱ በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን እሑድ ወይም የብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
· ለጨረታው የተዘጋጁትን ተሽከርካሪዎች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ ከ8ኛው ቀን ጀምሮ ከጧቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በአካል መመልከት ይቻላል፡፡
· የጨረታውን ሰነድ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፣
· ሰነዱ የተጫራቾች መመሪያ በዝርዝር አካቶ የያዘ ስለሆነ ፎርሙ ከመሞላቱ አስቀድሞ በጥንቃቄ ሊነበብ ይገባል፡፡
· የጨረታ ሰነዱ በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ተሽከርካሪዎች ዝርዝር እና የጨረታ ማስገቢያ ፎርም የያዘ ሲሆን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ ለመግዛት የሚወስኑትን ተሽከርካሪ ይለያሉ፣ ስሙንና የሠሌዳ/ኮድ ቁጥሩን ይይዛሉ፡፡
· ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የጨረታ ማስከበሪያ (ማስያዣ) የሞሉትን ዋጋ 10% ሲፒኦ CPO ማሲያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
· ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ፎርም ላይ በመሙላት እና የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ከተረጋገጠ ሲፒኦ ጋር አያይዘውና በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ጨረታው በይፋ ሊከፈት ግማሽ ሰዓት እስከሚቀረው ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
· ጨረታው በ15ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት በማዕከሉ የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0936019191) ወይም 0975264159 መጠየቅ ይቻላል፡፡
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር
