ዘመን ባንክ አ.ማ. በቁጥር 20 ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ሽያጭ ማስታወቂያ
ዘመን ባንክ አ.ማ. በቁጥር 20 ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ደንቦች፡-
1. ሞተር ሳይክሎቹን ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ሞተር ሳይክሎቹን “ጎፋ መብራት ኃይል ስኩል ኦፍ ቱሞሮ ት/ቤት አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ መመልከት ይችላሉ፤ ወይም በስልክ ቁጥር 0115-57-58-25/011 668 78 09 በመደወል ወይም ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው በባንኩ ዋናው መሥሪያ ቤት 12ኛ ፎቅ ላይ በንብረት እና ሎጂስቲክ አስተዳደር መምሪያ በአካል በመቅረብ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፤
2. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና የዋጋ መሙያ ቅጽ ከባንኩ የንብረት አስተዳደርና ሎጂስቲክስ መምሪያ በመግዛትና እና በመሙላት በጨረታ ሰነዱ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የመረጡትን ሞተር ሳይክል/ሎች ለመግዛት የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሕንጻ 12ኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
4. ጨረታው ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ላይ በባንኩ ሕንጻ 19ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
5. ጨረታው በሚካሄድበት ዕለትና ሰዓት መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው።
6. አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ለባንኩ ክፍያ መፈጸም አለበት፡፡ ይህን ባያደርግ ግን ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፤
7. ባንኩ ንብረቱን በገዢው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው የመንግስት አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
8. ከስም ዝውውር ጋር ያሉ ማናቸውንም ክፍያዎች፣ እንዲሁም ሞተሮቹን ከማስተካከል፤ ከመጫንና ከማጓጓዝ ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ክፍያዎች ገዢው ይከፍላል፡፡
9. ተጨማሪ የጨረታ ደንቦች የጨረታ ሰነድና የዋጋ መሙያው ቅጽ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
10. ባንክ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ዘመን ባንክ አ.ማ
