Tender Detail

Tender Details

  • Company Love in Action Ethiopia (LIAE)
  • Address , Phone: +251-910-49-12-33
  • Website
  • Deadline25 Jun 2026, 2:00 AM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document Price
  • opening date2026-06-25 02:30:00
  • Categories Vehicles Rent , Catering And Cafeteria Services

ላቭ ኢን አክሽን ኢትዮጲያ በመሆኑም ከስር በተዘረዘሩት የስራ ዘርፎች የተለያዩ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። LOT 1: በመሆኑም በአሁን ሰዐት በተለያዩ አከባቢዎች ለሚተገበሩ ፕሮጀክት የተለያዩ ስብሰባዎችን እናካሄዳለን። በዚሁ መሰረት ሆቴሎች አዳራሽ፣ የምሳ እና የሻይና ቡና አገልግሎት ለመስጠት የሚችሉ አዲስ አበባ፣ ቢሾፍቱ እና በሀረር ከተሞች የሚገኙ 4 ኮከብ እና 3 ኮከብ ሆቴሎችን አወዳደርን ውል በመግባት መስራት እንፈልጋለን። LOT 2: ድርጅታችን የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በሚያካሄድበት አከባቢዎች የመኪና ኪራይ አገልግሎት መስጠት የሚችል LOT 3: ድርጅታችን ለሚያካሂደው ማንኛውም የሆነ የሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ በረራዎችን ማመቻቸት የሚችል የጉዞ ወኪል


                               ላቭ ኢን አክሽን ኢትዮጵያ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ላቭ ኢን አክሽን ኢትዮጲያ በጤና፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ አቅም ግንባታ፣ በሰላም እና እርቅ ልማት፣ መልካም አስተዳደር እና በማህበራዊ ተጠያቂነት በማስፋት እና በማስረጽ፤ በድንገተኛ አደጋ ድጋፍ እና በመልሶ ማቋቋም፤ እና ሁለገብ የማህበረሰብ ድጋፍ ፕሮግራሞችን በመደገፍ ረገድ ከመንግስት እና ከተጠቃሚዉ ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት መጠነ ሰፊ ስራዎችን ላለፉት 25 አመታት በ ሁሉም ክልሎች ላይ ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል። በመሆኑም ከስር በተዘረዘሩት የስራ ዘርፎች የተለያዩ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

LOT 1: በመሆኑም በአሁን ሰዐት በተለያዩ አከባቢዎች ለሚተገበሩ ፕሮጀክት የተለያዩ ስብሰባዎችን እናካሄዳለን። በዚሁ መሰረት ሆቴሎች አዳራሽ፣ የምሳ እና የሻይና ቡና አገልግሎት ለመስጠት የሚችሉ አዲስ አበባ፣ ቢሾፍቱ እና በሀረር ከተሞች የሚገኙ 4 ኮከብ እና 3 ኮከብ ሆቴሎችን አወዳደርን ውል በመግባት መስራት እንፈልጋለን።

LOT 2: ድርጅታችን የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በሚያካሄድበት አከባቢዎች የመኪና ኪራይ አገልግሎት መስጠት የሚችል

LOT 3: ድርጅታችን ለሚያካሂደው ማንኛውም የሆነ የሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ በረራዎችን ማመቻቸት የሚችል የጉዞ ወኪል

ስለዚህ በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የታክስ መለያ (TIN) ማቅረብ የሚችሉ እንዲሳተፉ እየጋበዘን ዝርዝር የጨረታ መመሪያ እና ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 15 2018 ባሉት ተከታታይ የስራ ቀኖች በስልክ ቁጥር +251-910-49-12-33 ወይም በ liaebidliaebid@gmail.com ኢ-ሜል አድራሻ የጨረታ ሰነድ በመጠየቅ መውሰድ የምትችሉ ሲሆን፤ አቅራቢዎች የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ፕሮፖዛል liaebidliaebid@gmail.com እስከ ሰኔ 18 2018 ከጠዋቱ 8:00 ሰዐት ድረስ ማቅረብ ትችላላችሁ። ጨረታው ሰኔ 18 2018 ከጠዋቱ 8፡30 በዋና መ/ቤት ሁሉም ሰነዶች በኮሚቴው ይመረመራሉ።

በአካል በመቅረብ ጨረታውን ማስገባት የምትፈልጉ አቅራቢዎች ከስር በሚገኘው አድራሻችን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

አድራሻ፡ “ ሰሚት ከተባበሩት አደባባይ ወደ አቤም በሚወስደው መንገድ አሜሪካ ሜዲካል ሴንተር ገባ ብለው ባለው የግራው መንገድ ሰማያዊው የሰንሻይን አጥር እንደጨረሱ በስተግራ ባለው አስፓልት ስትታጠፉ በቀኝ በኩል ያለው ሶስተኛው ቤት

ለበለጠ መረጃ፡ በ 011-6-7-57-26/27 ወይም 0910-49-12-33 መደወል ይችላሉ።

ላቭ ኢን አክሽን ኢትዮጵያ ጨረታውን በከፊል እንዲሁም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

Save Tender

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ለብሩህ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት ለ2019 የተለያዩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

READ MORE
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት መጠቀሚያ የሚሆን በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሽ...

READ MORE
ETHIOPIAN SHIPPING AND LOGISTICS WOULD LIKE TO INVITE INTERESTED AND ELIGIBLE BIDDERS FOR PURCHASE O...

READ MORE