ጸደይ ባንክ አ.ማ ለወ/ሮ መሰረት ተሻገር ለሰጠው ብድር በዋስትና ያስያዘውን በደ/ማርቆስ ከተማ በካርታ ቁጥር k/አብ-01007 የተመዘገበ በአዋሳኝ በምስራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ያሳብ አያሌው፣ በሰሜን ዳዊት አያሌው፣ በደቡብ ሽበሽ ገላየ የሚያዋስነው ስፋቱ 150 ካ/ሜ የሆነ የመኖሪያ ቤትና ቦታ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በድጋሚ ለ2ኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ፡፡
ጸደይ ባንክ አ.ማ ለወ/ሮ መሰረት ተሻገር ለሰጠው ብድር በዋስትና ያስያዘውን በደ/ማርቆስ ከተማ በካርታ ቁጥር k/አብ-01007 የተመዘገበ በአዋሳኝ በምስራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ያሳብ አያሌው፣ በሰሜን ዳዊት አያሌው፣ በደቡብ ሽበሽ ገላየ የሚያዋስነው ስፋቱ 150 ካ/ሜ የሆነ የመኖሪያ ቤትና ቦታ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በድጋሚ ለ2ኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ኛ በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ በጸደይ ባንክ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ ፡፡
- የቤቱ ጨረታ መነሻ ዋጋው ብር 3,452,861.48 /ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ አምሳ ሁለት ሺ ስምንት መቶ ስልሳ አንድ ከአርባ ስምንት ሳንቲም/ ነው ፡፡
- በጨረታ የሚሳተፈው በህግ ሰውነት ያገኘ ድርጅት ከሆነ የድርጅቱን የጸደቀ የመመስረቻ ጽሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ፣ ህጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት ፡፡
- የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል ፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን ቀሪውን ገንዘብ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ በመክፈል ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል ፡፡ በዚህ ቀን ውስጥ ካልከፈለ ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው 1/4ኛ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል ፡፡
- በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል ፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያየዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ፣ግብር፣ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ፣እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጭዎችን ይከፍላሉ ፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዥው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡
- ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ ፡፡
- ጨረታው የሚካሄደው ደ/ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 13 ለጨረታ በወጣው ንብረት ውስጥ ነው ፡፡
- ጨረታው የሚካሄደው ሃምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912436868 / 0921667115 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ ፡፡
