የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ሙሉ ለሙሉ ክፍያቸው የተጠናቀቀ 04 (አራት) ኮንደሚኒየም ሱቆች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ እና በ2019 በጀት ዓመት ለክርስትና እምነት ተከታዮች የዳልጋ ከብት ሥጋ መሸጫ ሱቆችን /ኮንቴይነሮችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የኮንደምንየም የንግድ ሱቅ ሽያጭ እና የሥጋ መሸጫ ሱቆች ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ሙሉ ለሙሉ ክፍያቸው የተጠናቀቀ 04 (አራት) ኮንደሚኒየም ሱቆች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ እና በ2019 በጀት ዓመት ለክርስትና እምነት ተከታዮች የዳልጋ ከብት ሥጋ መሸጫ ሱቆችን /ኮንቴይነሮችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች፡-
- ኮንደሚኒየሞቹ አዲስ አበባ በሚገኙ አራት ክፍለ ከተማዎች የሚገኙ ሲሆኑ ያሉበት ሁኔታ እና የእያንዳንዱን የንግድ ሱቅ ስፋት ከጨረታ ሰነዱ ማግኝት ይቻላል፡፡
- ለጋራ መኖሪያ ኮንደሚኒየም ንግድ ሱቅ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጨረታ ቀን ድረስ የንግድ ሱቆች በሚገኙበት ሳይት በመገኝት ማየት ይቻላል፡፡
- ለዳልጋ ከብት ስጋ መሸጫ ሱቆች ኪራይ በተመለከተ በመስኩ ወይም በተመሳሳይ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑ ግብር የከፈለ የማይመለስ ኮፒ በማያያዝ ማቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ/ ቢድ ቦንድ/ ለኮንደሚኒየም ሱቆች ሽያጭ ለእያንዳቸው ከተ.እ.ታ በፊት የሚገዛበትን ዋጋ 10% እና ለዳልጋ ከብት ስጋ መሸጫ ሱቅ ኪራይ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲፒኦ ገቢ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለኮንደሚኒየም ሱቆች የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ እና የዳልጋ ከብት ሥጋ መሸጫ ሱቆች ኪራይ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘውን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎኘ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- ጨረታው ለዳልጋ ከብት ሥጋ መሸጫ ሱቆች /ኮንቴይነሮች/ ኪራይ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 እና ለኮንደሚኒየም ሱቆች ሽያጭ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋት 4፡15 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 01114-163978 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
