ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ፡- Bank 45 GSM 82 or 84 CM roll paper, Bank 45 gsm 61X86 white paper and bond 60 gsm 61X86 white paper በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሀገር ውስጥ የግዥ ጨረታ ሰነድ
ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ፡- Bank 45 GSM 82 or 84 CM roll paper, Bank 45 gsm 61X86 white paper and bond 60 gsm 61X86 white paper በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ሰርተፊኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ድረስ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሮአችን መግዛት ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋቸውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ አሽገው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከግዥ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ።
5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በማህበሩ የስብሰባ አዳራሽ/የግዢ ክፍል ይከፈታል። 15ኛው ቀን በዝግ ቀን ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
6. ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
ስልክ ቁጥር ....... 011 515 50 05/ 011 551 88 72
ፋክስ ...... 011 551 86 96
ፖ.ሳ.ቁጥር ...... 2365
ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
አዲስ አበባ
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
