Tender Detail

Tender Details

  • Company የፍልዉሃ አገልግሎት ድርጅት
  • Address Addis Ababa Ethiopia, Phone: 0115 53 07 67
  • Website
  • Deadline14 Jul 2026, 10:28 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-07-14 10:30:00
  • Categories Cosmotics

ፍልውሃ እገልግሎት ድርጅት የመታሻ ዘይት /ፖራፊን ኦይል/ እቃ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


 

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጫረታ ማስታወቂያ

 

ፍልውሃ እገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት፡-ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የዕቃ የአገልግሎት ግዥ

 ሎት 1 የመታሻ ዘይት /ፖራፊን አይል/ አቅርቦት ግዥ

ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች በማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው

1.     ተጫራቾች በዘርፋ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ 2018 . ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2.     ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው፤የገቢዎች ከሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3.     ማንኛውም ተጫራች የግዥ የጨረታ ማስከበሪያ 25.000.00/ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።

4.     ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

5.     ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6.     ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት። ስለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት።

7.     ጨረታውን በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የስጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል።

8.     ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል።

9.     ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 07/2018 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 430 ይከፈታል።

10.ተጫራቾች በሚጫረቱበት የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴከኒካል ሰነድ እና ፋይናሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁን ማስገባት ይኖርባችኋል። የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ለብቻው እና ፋይናሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባ አለባቸው።

11.የጨረታ ሂደቱ የቴከኒክ ሰነድ ግምገማ እና ናሙና ጥራት ግምገማ ውጤት (40%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60%) ሲሆን ድምር ውጤት አሸናፊ የሚለይመሆኑን ማወቅ አለባችሁ። ነገር ግን ቴክኒካል፣ ናሙና ጥራትና ብቃት ግምገማ ያላለፈ ተጫራች ፋይናንሽያል ሰነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ። የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ላይ ማየት ይቻላል።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።ስበስጠ መረጃ፦ ስልክ ቁጥር 0115 53 07 67/011 5 15 73 37

 

የፍልውሃ አገል ግሎት ድርጅት

 

Save Tender