Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢያዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይከል እና የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት ዕቃዎች፤ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመገናኛ መሣሪያዎች ኮስሞቲከስ እና የንፅሕና መጠበቂያ ዕቃዎች፤ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፤ ነዳጅ፤ ምግብ ነክ ዕቃዎች፤ የጥራጥሬ እህሎች እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ


የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ


በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢያዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይከል እና የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት ዕቃዎች፤ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመገናኛ መሣሪያዎች ኮስሞቲከስ እና የንፅሕና መጠበቂያ ዕቃዎች፤ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፤ ነዳጅ፤ ምግብ ነክ ዕቃዎች፤ የጥራጥሬ እህሎች እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ሟሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
1. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃዎች ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የንግድ ፊቃድ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስከርወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
2. ተጫራቾች የግልጽ እና የሐራጅ ጨረታ ሰነድ በቴሌግራም አካውንት የሚላከላችሁ ሲሆን ተጫራቹ ለመግዛት የሚፈልገውን የዕቃ ዝርዝር ያለበት ገጽ እና የጽ/ቤቱ ማኅተም ሳይቆረጥ ፕሪንት በማድረግ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡00-12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ግልጽ እና ሐራጅ ሰነድ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በጽ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁጥር 16 ሰነድ የገዛበትን ደረሰኝ (RV) በመቀበል ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ ሌሎች ከላይ የተገለጹ አስፈላጊ ሰነዶች እንዲሁም RV (ሰነድ የተገዛበት ደረሰኝ) ጭምር በማያያዝ ወደ ጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
3. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሐራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ ማስያዝ ያለባችሁ የሲ.ፒ.ኦ መጠን በየኮዱ የሚለያይ ስለሆነ ከጨረታ ደንብ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በጉምሩከ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ጨረታው የሚካሄደው በሞያሌ ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል።
5. ተጫራቾች ማስታወቂያ በጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እስከ 7ተኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መ/ጣቢያ የሚገኙ መጋዘኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው፡፡
6. ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሦስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ) ተዘግቶ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል፡፡
7. ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን የሥራ ቀን ሳይሆን ሲቀር ጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
8. ለጨረታው አሽናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታውን ውጤት ከተገለጸ በ 3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
9. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት CPO ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭይቀርባል።
11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0464441415/0464441564 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።


በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Sale of seized and inherited goods by Ethiopian Customs Commission, Moyale Branch: motorcycles, vehicle spare parts, clothing, electronics, cosmetics, fuel, food, grains, and more via open and auction tender. Bidders need valid trade license, VAT registration, and tax clearance.
Save Tender