አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበር Sony Camera a7 v እና አክሰሰሪዎች በግልፅ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር: AWACH/NCB/G/02/2018/26
አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበር Sony Camera a7 v እና አክሰሰሪዎች በግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተወዳዳሪዎች/ ተጫራቶች:-
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ከገቢዎች ሚኒስቴር በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
2. በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የምዝገባ ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል እዋሬ፣ ሴቶች አደባባይ በሀብትሽ አውቶሞቲቭ ገባ ብሎ ወደ አደዋ ድልድይ በሚወስደው መንገድ ላይአጋር ሕንጻ፣ 2ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 201 በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ካሜራና እከሰሰሪዎች በሙሉ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን እንዲሁም የድርጅቱን ማህተም አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
8. በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
9. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣ ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዶቻቸውን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዚሁ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
10. ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስበስጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-557-7341 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ስድራሻ፡- አዋሬ፣ ሴቶች አደባባይ በሀብትሽ አውቶሞቲቭ ገባ ብሎ አደዋ ድልድይ፣ አጋር ሕንጻ፣ 2ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 201
አዋጭ የገ/ቁ/ብ/ኃሳ/የተ/መሠ/የህ/ስ/ ማህበር ዋና ቢሮ
