ዲ.ኤም.ሲ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ማህበር በ65,395ካሬ ሜትር ላይ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለቡ መብራት ኃይል አካባቢ የዲ.ኤም.ሲ ሪል እስቴት ህንጻዎች ግንባታዎች በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም ምክንያት 20,000ኪዩቢክ ሜትር የሚሆን የአፈር ማውጣት (Cart away) ስራዎችን በጨረታ አወዳድሮ በተጫራቾች ማሰራት ይፈልጋል።
ድርጅታችን ዲ.ኤም.ሲ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ማህበር በ65,395ካሬ ሜትር ላይ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለቡ መብራት ኃይል አካባቢ የዲ.ኤም.ሲ ሪል እስቴት ህንጻዎች ግንባታዎች በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም ምክንያት 20,000ኪዩቢክ ሜትር የሚሆን የአፈር ማውጣት (Cart away) ስራዎችን በጨረታ አወዳድሮ በተጫራቾች ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት ከታች በተገለጹት ቀናቶች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የጨረታው መስፈርቶች
- በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ
- ታደሰ ንግድ ፍቃድ (Trading license renewed for 2017E.C)፣
- ቫት ምዝገባ ሰርተፊኬት (VAT registration certificates)፣
- ቲን ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN registration certificates)፣
- ታክስ ክሊራንስ ሰርተፊኬት (Tax Clearance Certificate)፣
- የኮንስትራክሽን ፍቃድ ሰርተፊኬት (Certificate of registration from Ministry of Works and Urban Development) እና
- የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፊኬት (Registration as supplier in the list of the mandated public body, i.e. Public Procurement and Property Administration Agency (PPPAA) ግዴታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ለስራው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ማቅረብ አለባቸው፤ ተጫራቾች ለስራው የሚያስፈልጉ መኪኖች፣ ማቴሪያልና የሰው ኃይል ማለትም ገልባጭ መኪናዎች ከነሹፌሮቹ፣ ለመኪኖች የሚያስፈልግ ነዳጅ፣ ሰርቪስ ዘይቶችና የመሳሰሉትና የአፈር መድፊያ ቦታ (Spoil Area) ተጫራቹ ማቅረብ ይኖርበታል፤ ኮንትራክተሩ ለስራው የሚያስፈልግ አፈር መቆፈሪያ ማሽን (ኤክስካቫተር) ብቻ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በአፈር ማውጣት ስራ (Cart away) ላይ የስራ ልምድ (Experience) ያላቸው መሆን የሚገባቸውና የስራ ልምድ ማስረጃዎችን ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታውን ላይ ጥያቄ/ማብራሪያ ካላቸው ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00LT-11፡00LT ሰዓት ዲ.ኤም.ሲ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ.ማህበር ዋና መስሪያ ቤት አዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ለቡ መብራት ኃይል 2ኛ ፎቅ ላይ በመገኘት ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች በስልክ ቁጥር 0975067100/0974096900 የሚፈልጉትን መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ጨረታ ሰነድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንቶች በሁለት የተለያዩ ፖስታዎች የሚታሸጉ ሲሆን በስተመጨረሻም ሁለቱ ዶክመንቶች በአንድ ፖስታ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንቶች ተብሎ የሚታሸግ ይሆናል፡፡ ከቴክኒካል ዶክመንት ጋር የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 25,000 (ብር ሃያ አምስት ሺህ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ቴክኒካል ዶክመንት ህጋዊ ዶክመንቶች (Legal Documents)፣ የስራ ልምድ (Experience)፣ የንብረት ባለቤትነት ማስረጃዎች (Dump Trucks Ownership Certificate) እና የአንድ አመት ፋይናንሻል ሰነድ (Financial Statement) ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታ ሰነድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንቶች የተጫራች ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በአንድ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከናወነው ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ስድስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሆኖ የጨረታ ሰነዱ ተጫራቾች ጥቅምት 13 2018ዓ.ም. ከሰአት በኃላ ከ9፡00LT ሰዓት በፊት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ጨረታው የተጫራች ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት 9፡30LT 10ኛ ፎቅ ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ2 ቀን ውስጥ ወደ ስራ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ፋይናንሻል ፕሮፖሳል ከዚህ በታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ የሚሞላ ይሆናል፡፡
ተ.ቁ |
የሥራ ዝርዝር |
መለኪያ |
መጠን |
ነጠላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ |
ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ |
1 |
የአፈር ማውጣት ስራ (Cart away) |
በሜትር ኪዩብ (m3) |
32,000 |
