Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ተሽከርካሪ እና ያገለገሉ ሞተርሳይክሎችን በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የሐራጅ ጨረታ ቁጥር 22/2018 .

 

በኢትዮጵያ ጉምሩ ኮሚሽን የአዳማ //ቤት በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ከርካሪ እና ያገለገሉ ሞተርሳይክሎችን በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑንእየገለጽን፡-

በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

1.     ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ ክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡

2.     በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡

3.     የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በሥራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት 200-600 ሰዓት መመልከት ይቻላል፡፡

4.     ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና የሚያበቃበት እንዲሁም ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ፡-

 

.

የዕቃው አይነት

የጨረታው አይነት

በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን

ጨረታው የሚጀምርበት ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት

ስልክ ቁጥር

1

ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች

ሐራጅ

17/10/2018

22/10/2018

400

800

0221118429/0222118925

2

ተሽከርካሪ

ሐራጅ

17/10/2018

22/10/2018

400

800

0221118429/0222118925

3

ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች

ሐራጅ

17/10/2018

22/10/2018

400

800

0221118429/0222118925

 

5.     በጨረታው ሽያጭ የዕቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም፡፡

6.     በጨረታው ላይ የወጡት ሞተር ሳይክሎች እና ተሽከርካሪ ማንኛውም ዕድሜው 18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ሳያስፈልገው በታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ብቻ በኦከሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ መጫረት ይችላል፡፡

7.     በሐራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ለጨረታው ዋስትና የሚሆን ማለትም፤ ለምድብ 01, ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 331,200.00 ለምድብ 02, ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 28,000.00 ለምድብ 03, ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 193,700.00 ለምድብ 04, ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 768,400.00 ለምድብ 05, ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 539,000.00 ለምድብ 06, ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 1,406,400.00 ለምድብ 07, ተሸከርካሪ  መለዋወጫዎች ብር 934,000.00 ለምድብ 08, ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 781,500.00 ለምድብ 9, ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 129,400.00 ለምድብ 10, ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 186,500.00 ለምድብ 11, ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 684,000.00 ለምድብ 12, ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 102,700.00 ለምድብ 13, ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 618,700.00 ለምድብ 14, ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 109,500.00 ለምድብ 15, ተሸከርካሪ ብር 216,710.00 ለምድብ 16, ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ብር 25,000.00 እና ለምድብ 17, ሞተርሳይክሎች 10,000.00 (Customs Commission Adama Branch) ስም ብቻ ... በማሠራት ያሠሩትንም ... በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡

8.     በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡትን እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ /ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 እንዲሁም ተሽከርካሪው በከልቻ ግቢ መጋዘን ቁጥር 10 ውስጥ ሚገኙ ሲሆን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 6 ስድስተኛው ቀን 400 ሰዓት ጀምሮ ኦንላይን ላይ ለየምድቦቹ በተሰጠው ሰዓት መሰረት መጫረት ይቻላል፡፡

9.     በሐራጅ ጨረታ የእቃዎቹ የመነሻ ዋጋ ያልተወሰነላቸው ስለሆነ የመነሻ ዋጋ በተጫራች የሚሰጥ ይሆናል፡፡

10. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለጸ 3 /ሶስት/ የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

11. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

12. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም፡፡

13. ከላይ በተ/ 9 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

14. //ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

15. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሠሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡

 

NB:- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መረጃዎች ያላሟሉ ተጫራቾች ቢያሸንፉ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ ለመንግሥት ገቢ የሚደረግ እና እቃው በድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-55-11/ 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- አዳማ ///ቤት የውርስ መጋዘን የሥራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች

0221118429 እና 0222118925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ //ቤት

Save Tender