Tender Detail

Tender Details

  • Company ታህሰብ የንግድ ሥራዎች አክሲዮን ማህበር
  • Address አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኮልፌ አጠና ተራ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0112-79-30-65
  • Website
  • Deadline10 Jul 2026, 3:28 PM
  • magazineAdiss zemen
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-07-10 15:28:00
  • Categories Steel, Metals And Aluminium , Lead Glass And Mirror

ታህሰብ የንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበሩ ያገለገሉ ብዛት ያላቸው በሮች፤ መስኮቶች እና ሌሎች የተለያዩ ብረታ ብረቶች እና መስታወቶች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ


ታህሰብ የንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበሩ ያገለገሉ ብዛት ያላቸው በሮች፤ መስኮቶች እና ሌሎች የተለያዩ ብረታ ብረቶች እና መስታወቶች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
1. የዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ቁጥር ያለው፤
3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ15 (አስራ አምስት) ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከቀኑ 3፡00 አስከ 10፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ እስከ 5፡30 ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል ብሎክ 8 አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸ በተገኙበት በአክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
5. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ በማድረግ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
6. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ዋስትና) በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ብር15,000.00 (አስራ አምስት ሺ ብር) በአከሲዮን ማህበሩ ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር መመለስ ይኖርበታል፡፡
8. የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት (ግለሰብ) በውስጥ ማስታወቂ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በራሱ ወጪ ማንሳት ይኖርበታል፡፡
9. አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡


ለበለጠ ማስረጃ ስልክ ቁጥር 0112-79-30-65
ታህሰብ የንግድ ሥራዎች አክሲዮን

Save Tender