በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዲስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት ለኢንጅነሪንግ ሥራ ለምርት ሥራ እጋዥ የሆኑ የተለያዩ መካኒካል ማሽኖች እና የሲሲቲቪ ካሜራና ተያያዥ ዕቃዎች አቅርቦት፣ ገጠማና ዝርጋታ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ጨ.ሰ.ቁ:- NCB- AAMMI-005/2018
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዲስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት ለኢንጅነሪንግ ሥራ ለምርት ሥራ እጋዥ የሆኑ የተለያዩ መካኒካል ማሽኖች እና የሲሲቲቪ ካሜራና ተያያዥ ዕቃዎች አቅርቦት፣ ገጠማና ዝርጋታ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት-1 የተለያዩ መካኒካል ማሽኖች
ሎት-2 ፡ የሲሲቲቪ ካሜራና ተያያዥ
ዕቃዎች አቅርቦት ገጠማና ዝርጋታ ሥራ
➢ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ያህል ሰነዱን አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 014 በመገኘት መውሰድ (መግዛት) ይችላሉ፡፡
➢ ተጫራቶች ከሚያቀርቡት እቃ ጋር ተዛማጅ የሆነ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ የምስከርወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብርየከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የግብር ከሊራንስ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ/ የሚያስችል ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
➢ ተወዳዳሪዎች በጨረታው ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ መመሪያው ላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው:: የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተጫራቹ ምርጫ ከሚከተሉት ዓይነቶች አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡
(ሀ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና፣
(ለ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም የከፍያ ትዕዛዝ /CPO/ የባንከ ጋራንቲው 60 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፣
➢ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስርየስራ ቀን) ቀናት በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዢ ከፍል ቢሮ ቁጥር 014 በመገኘት ሰነዱን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተገለፀው አስተሻሸግ መሠረት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
➢ ጨረታው የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር የሥራ ቀናትን አልፎ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከረፋዱ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተገለፀው አድራሻ በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የስብሰባ አዳራሽ ጨረታው ይከፈታል፡፡ ቀኑ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡ የተጫራች አለመኖር ፖስታው ተሟልቶ እስከተገኘ ድረስ ጨረታውን ለመከፈት እያስተጓጉልም፡፡
➢ ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 022110689/0912264680 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡-አዳማ ከወንጂ ማዞሪያ ተቃራኒ ስቅጣጫ 500ሜ ላደ វាព:-0221110689/0912264680 ፋስክ:-0221111866
አዳማ
በኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
