Tender Detail

Tender Details


እንግሊዝ ኤምባሲ- የነዳጅ ታንከር፣ ጀነሬተሮች፣ ኮነቴንሮች፣ ፕሪንተር እና ስካነሮች፣  እንዲሁም የተለያዩ ቁርጥራጭ እቃዎችን በጨረታ ማስተላለፍ ይፈልጋል።


የእንግሊዝ ኤምባሲ፣ አዲስ አበባ የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲ- የነዳጅ ታንከር፣ ጀነሬተሮች፣ ኮነቴንሮች፣ ፕሪንተር እና ስካነሮች፣  እንዲሁም የተለያዩ ቁርጥራጭ እቃዎችን በጨረታ ማስተላለፍ ይፈልጋል።

የጨረታ ዝርዝሮች፦

  • መመልከቻ እና የጨረታ ቀን፡ 17 ሃምሌ 2017 | 3:00 ጠዋት – 10:00 ከሰዓት
  • የውጤት ማስታወቂያ ቀን፡ 21 ሃምሌ 2017
  • የእቃ መረከቢያ ቀን፡ ሃምሌ 23 – 24 2017 | 3:00 ጠዋት – 10:00 ከሰዓት
  • ቦታ፡ በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ

ለመመዝገብ

እቃዎቹን ለማየት እና ለመጫረት፣ ከዚህ በታች በተገለጸው ሊንክ በመጠቀም እስከ ፤ ሃምሌ 15 2017፤ 11:00 ሰዓት ድረስ መረጃዎትን በማስገባት ይመዝግቡ፦

https://forms.cloud.microsoft/e/Ef8W057vt8

የጨረታው ሂደት የሚከናወነው ጨረታው በሚደረግበት ዕለት በሞባይል ስልክዎ ስካን በሚደረግ (QR) ኮድ መሰረት በሚያቀርቡት የግል ጨረታ  ዋጋ አማካኝነት ይሆናል።

የተሳትፎ መስፈርቶች:

  • ተሳታፊው በህግ የተፈቀደለት የጨረታ ተሳታፊ መሆን አለበት።
  • ተሳታፊዎች ማንነትቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዝው መገኘት ይኖርባቸዋል።
  • የውጭ ተሳታፊዎች በጨረታው ለመሳተፍ የማይመልሰ 5000 ብር በጥሬ ገንዘብ መክፈል ይጠበቅባቸዋል።
  • ለውጭ ተሳታፊዎች በኤምባሲው ውስጥ ወይም ዙሪያ ተሽከርካሪ ማቆም አይፈቀድም፡፡ በመሆኑም ተስማሚ የማቆሚያ ቦታ የመፈለግ ሃላፊነት የተሳታፊዎች ይሆናል፡፡

ማስታወሻ፡

  • ሁሉም እቃዎች እንደሚታየው ይሸጣሉ. የእንግሊዝ ኤምባሲ የማንኛውንም ዕቃ ሁኔታ ወይም ተግባር በተመለከተ ምንም አይነት ዋስትና አይሰጥም እና ለስራ ሁኔታቸው ምንም አይነት ሃላፊነት አይቀበልም።
  • ተሳታፊዎች ካሸነፉበት ጨረታ ውስጥ ነጠላ እቃዎችን መምረጥ ወይም ውድቅ ማድረግ አይችሉም።
  • የእንግሊዝ ኤምባሲ የጨረታውን ሂደት በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

የእንግሊዝ ኤምባሲ፣ አዲስ አበባ
ኮሞሮስ መንገድ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Save Tender