Tender Detail

Tender Details


መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ የሰነድ ቁጥር 127

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ቁሳቁሶቹም:

1. የመኪና መለዋወጫዎች

2 ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

3. የመዋኛ ልብሶች

4. የተነቃቀሉ ጣውላዎች

5. ቋሚ የመብራት ፖል (ምሰሶዎች)3 ጊዜ

6. አሮጌ ጎማዎች ናቸው::

7. ከፍልፋይ ያለው የምግብ ሳህን( ስቲልነስ ስቲል)

በመሆኑም ተወዳድሮ መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚኩራ ከፍለ ከተማ ወረዳ 03 (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተከርስትያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቁሳቁሶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ከፍል ድረስ በመምጣት ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡የጨረታ ሰነዱ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር የያዘ ሲሆን ዕቃዎቹን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ በሰነዱ በእያንዳንዱ ቁጥር አንፃር የተለዩትን ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት እና ዕቃውን ለመግዛት ያስገቡትን ዋጋ 10% ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ጋር በማያያዝ ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በክኛው ቀን ከጠዋቱ 430 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 500 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ከኛው ቀን እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ!!

ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0930-79-64-13 ወይንም 0975-26-41-59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

 

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር

Save Tender