Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተወረሱ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


በጉምሩክ ኮሚሽን

የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

የተተዉና ተወረሱ ዕቃዎች የሀራጅ ቸረታ ቁጥር ሐ-49/2018ጨረታ

 

በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ /ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር1160/2011 እንቀፅ 13 ንዑስ እንቀፅ ( መሰረት አስመጭዎች ዕቃቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጉምሩከ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተው የተቆጠሩ እና በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 10 መሠረት የተተው ንብረቶችን ማለትም LABORATORY STOOL CHAIR, የስቴሽነሪና የማስታወቂያ እቃዎች : CONNECTING HOD: BLADE FUSE የተለያዩ ሽቶዎች እቃዎች VBRATION ANALYSIS OF CENTRIEUGAL FAN እና የተሸከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1) ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነትእና ብዛት በማስታወቂያ ሠሌዳ እና በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 200 እስከ ቀኑ 600 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 700 እስከ ቀኑ 1030 እና ዓርብ ከጠዋት 200 እስከ ቀኑ 500 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 730 እስከ ቀኑ 10:30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 200 እስከ ቀኑ 5:30 መመልከት ይቻላል፡፡

2) ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ /ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው:: ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ፡፡

3) ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ዘርፉ በሚፈቅደው ብር300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርጫፍ /ቤቱ ሥም ETHIOPAN CUSTOMS COMMSSON MODJO BRANCH OFFICE በሚል  ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ አዳማና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት፡፡

4) የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአምስት (5) ተከታታይ ቀናት እየር ላይ ከዋለ በኋላ በፀኛው የሥራ ቀን በዚሁ ዕለት ጠዋት 500 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ /ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ የሚከፈት ሆኖ ማንኛውም ተጫራች እስከ 445 ሰዓት የሚጫረትበትን ዕቃ ለይቶ እቃ አወጋገድ ቡድን ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል፡፡

5) ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፣ ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም፣ የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ /ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡

6) የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት:: 5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡

7) በተራ ቁጥር 06 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ዕቃው 2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል፡፡

8) አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል፡፡

9) ቅርንጫፍ /ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

10) ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-90-94 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender