ፀደይ ባንክ አ.ማ አቶ ገረመዉ አይናለም ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዘዉን በምስራቅ ጎጃም ቀራንዮ ከተማ ቀበሌ 01 የካርታ ቁጥር K-926 በአቶ ገረመዉ አይናለም ስም ተመዝግቦ የሚገኘዉን የመኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ጫረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለመጀመርያ ጊዜ የወጣ የኃራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ አቶ ገረመዉ አይናለም ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዘዉን በምስራቅ ጎጃም ቀራንዮ ከተማ ቀበሌ 01 የካርታ ቁጥር K-926 በአቶ ገረመዉ አይናለም ስም ተመዝግቦ የሚገኘዉን የመኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ጫረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸዉ በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ መጫረት እንዲችሉ ይጋብዛል፡-
- የቤቱ የጫረታ መነሻ ዋጋ ብር427,438.65 (አራት መቶ ሃያ ሰባት ሽህ አራት መቶ ሰላሳ ስምንት ከ 65 ብር ብቻ የሆነ
2.ተጫራቾች የቤቱን ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር ¼ (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ) በጸደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጫረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
3.የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጫረታዉ ዉጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠዉ ብቻ ይሆናል፡፡
4.በጫረታዉ የሚሳተፈዉ በህግ ሰዉነት ያገኘ ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክልና ማቅረብ አለበት፡፡
5.የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጫረታ ያሸነፈዉን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨራታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
6.በጫረታዉ ለተሸነፉ ተጫራጮች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል፡፡
7.የጫረታ አሸናፊዉ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዙ ማናቸዉም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ማንኛዉንም ወጭዎች ገዢ ይሸፍናል/ ይከፍላል/፡፡ ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር እንዲዋዋል ይደረጋል፡፡
8.ተጫራቾች ቤቱን /ድርጅቱን/ በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
9.ጫረታዉ የሚካሄደዉ ሀምሌ 27/2018 ከጠዋቱ 3.00—5.00የተጫራቾች ምዝገባ፤ ከ5.00 እስከ ቀኑ 6.00 ጫረታ በደበረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 02 ዲስትሪክት 03ኛ ፎቅ ይሆናል፡፡
10.ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጫረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠተበቀ ነዉ፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ፡- ፀደይ ባንክ ደበረማርቆስ ዲስትሪክት ስ.ቁ 0587712034/ ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
