ሲንቄ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ቀጥሎ የቀረበዉ ንብረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ቁጥር ሲባ/ህአዲ/ሐራጅ/035/2018
| ተ | የተበዳሪ ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪ ቅርንጫፍ | ለጨረታ የቀረበው ንብረት መግለጫ | የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር
|
ጨረታው የሚከናወንበት | ጨረታው የወጣው | |||
| ቀን | ሰዓት | |||||||||
| 1
|
ጌትነት መገርሳ ጪብሳ | ጌትነት መገርሳ ጪብሳ | ኦዳ | ሱዙኪ እስዊፍት
ሞዴል 2022 |
AA-02-C29379 | MBHCZC63S00B41169 | 1,824,000 | 24/11/2018 | 4፡30-5፡30 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
ሲንቄ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ቀጥሎ የቀረበዉ ንብረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
የሐራጁ ደንቦች፤
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል የጨረታውን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአሥራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካል ከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- በሐራጁ ሂዳት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች ማን እንደሆነ ብቻ የሚገለፅ ሲሆን ጨረታውን ያሸነፈው ሰው/አካል ስለማሸነፉ በሚመለከተው የባንኩ አካል ከተረጋገጠ በኃላ ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ይሰጠዋል::
- ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል፡፡
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው::
- ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ፤ ካዛንቺስ የምገኘዉ ሲንቄ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 7ኛ ፎቅ ይሆናል፡፡
- በጨረታዉ ቀን ከ4፡30 እስከ 5፡00 የተጨራቾች ምዝገባ ሰዓት ሲሆን፣ ከ5፡00 ሰዓት በኋላ የተጫራች ምዝገባ አይኖርም። ከ5፡00 – 5፡30 ሐራጁ የሚካሄድበት ጊዜ ይሆናል።
- ለስም ዝውውር የሚከፈል ክፍያ እንዲሁም የሊዝ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ከታክስ እና ግብር ጋር ተያያዥ የሆኑ ክፍያዎችን ገዢው/አሸናፊው ይከፍላል:
- የንግድ ማህበራትን በመወከል መጫረት የሚፈልግ ማንኛዉም ግለሰብ የማህበሩን ህጋዊ ሰዉነት ያለዉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የመመስረቻ ወይም እና የመተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ህጋዊ የዉክልና ስልጣን ሰነድ ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለሐራጅ የቀረበ ንብረትን ለመጎብኘት የሚፈልግ ከአበዳሪ ቅርንጫፍ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራች የጨረታ አሸናፊ ነዉ የሚባለዉ አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በፅሑፍ ሲደርሰዉ ነዉ፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ የሲንቄ ባንክ ህግ አገልግሎት ክፍል ስልክ ቁጥር (+251-11557-6016), ፤ ኦዳ ቅርንጫፍ (0115571965) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ሲንቄ ባንክ አ.ማ
