Tender Detail

Tender Details


አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና 216/1992 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 1147/2012 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የሐራጅ ማስታወቂያ

ተ.ቁ  

የተበዳሪው ስም

 

የአስያዥ ስም

አበዳሪ ቅርንጫፍ የንብረቱ አድራሻ የቦታው ስፋት( በካሬ ሜትር) የባለቤትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የንብረቱ ዓይነት የጨረታ መነሻ ዋጋ ጨረታው የሚከናወንበት ቦታ፣ቀን እና ሰዓት
ከተማ ¡/Ÿ}T ወረዳ የቤ.ቁ
1 ማክሮ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እና ትሬዲንግ  ኃ/የተ/የግ/ማህበር ማክሮ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እና ትሬዲንግ  ኃ/የተ/የግ/ማህበር ካዛንችስ አዲስ አበባ ን/ስ/ላፍቶ 12 2500 AA000081200277 የኢንዱስትሪ አገልግሎት (G+1 የቢሮ ሕንፃ፣ መጋዘን) 75,376,988.28 ጨረታው የሚከናወነው በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ድረስ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋአንድ አራተኛ (1/4) ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) ብቻ በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ/ማ ስም በማሰራትና ለጨረታ ማስከበሪያነት በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  2. ጨረታው የሚካሄደው 22 አካባቢ በሚገኘው ሌክስ ፕላዛ ሕንፃ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይሆናል።
  3. የተጫራቾች ምዝገባ የሚከናወነው በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ 4፡00 – 5:30 ድረስ ይሆናል። ምዝገባውከተጠናቀቀ በኋላ ለንብረቱ የሚመደበው የጥሪ  ሰዓት  30  ደቂቃ ብቻ ሲሆን የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል።
  4. በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ከሚያካሂደው የባንኩ የህግ አገልግሎት መምሪያ ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
  5. የጨረታው አሸናፊ ቀሪውን ገንዘብ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል።
  6. የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ ይከፍላል፡፡
  7. ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል፡፡
  8. በሐራጅ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዥ ወይም የነዚህ ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡ ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዦች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታዉን ሂደት ለመከታተል በተጠቀሰዉ ቦታ እና ሰዓት እንድትገኙ እያሳሰብን ካልተገኛችሁ በሌላችሁበት ጨረታው የሚከናወን መሆኑን እንገልፃለን።
  9. ባንካችን ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል።
  10. ከሚሸጠው ንብረት ጋር የተያያዙ ከጨረታው በፊትም ሆነ በኋላ ማንኛውም ለመንግስት ሊከፈሉ የሚገባቸው የሊዝ ክፍያዎች፣ ወጪዎች ወይም ግብር እንዲሁም በንብረት ማስተላለፍ ሂደት የሚመጡ ማንኛውም አይነት ክፍያዎች ወይም ግብር ሙሉ በሙሉ የጨረታ አሸናፊው/ገዥው/ የሚሸፍን ይሆናል።
  11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ለበለጠ ማብራርያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት መምሪያ በስልክ ቁጥር 011-662-7120 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. 

Save Tender