አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድሰመክ/ብግጨቁ/11/2018 የሰራተኞች መዝናኛ ክበቦቹን በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በማወዳደር በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድሰመክ/ብግጨቁ/11/2018 የሰራተኞች መዝናኛ ክበቦቹን በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በማወዳደር በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-
1. በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade License)
2. የታክስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣
3. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በማቅረብ በግልዕ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ። በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት(6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት (ማዕከል) 8ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ህጋዊ ሰነዶች፣ የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ ማስከበሪያ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ 8ኛ ፎቅ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ 10ኛ ፎቅ ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፤
ድርጅቱ የተሻስ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡ 09 22 53 60 49
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት
