አዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ያገለገለ ጎማ እና ፊልትሮ፣አየርማጣሪያ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ያገ/ን/ሸ/ግጨ/007/2018
አዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በሰንጠረዥ የተገለፁትን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የሚሽጠው ዕቃ (አገልግሎት) አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
የጨረታ ሰነድ መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ ሰነድ መክፈቻ ቀንና ሰዓት
|
|
1 |
ሎት 1፡-ያገለገለ ጎማ |
በሚወዳደሩበት ሎት የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10% |
ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡00
|
ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡30
|
|
2 |
ሎት2፡-ፊልትሮ፣አየርማጣሪያ |
በሚወዳደሩበት ሎት የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10% |
ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡00
|
ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡30
|
ስስሆነም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-
1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ አለበት፡፡
2. ተጫራቾች 22 በሚገኘው ኢየሩስ ህንፃ የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ደርጅት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08 በመምጣት ለሽያጭ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑዘ፡ዐዐ ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡ oዐ ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን በሚገኙበት ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት ፡ የካ ቅ/ጽ/ቤት ፣ ሰሚት ቅ/ፅ/ቤት ፣ ሸጎሌ ቅ/ጽ/ቤት እና መካኒሳ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች በሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ ሎት የሎቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡
4. የጨረታ ሳጥኑ ሐምሌ 28/2018ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ሃያ ሁለት ኢየሩስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመከፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይካልሆነ (እሁድ ላይ ከዋለ) ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል፡፡
5. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት 22 ኢየሩስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0116-66-33-67 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት
