በለሚ ኩራ ከ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 8 እሞራው መታሰቢያ ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት አመት ከዚህ በታች የተቀመጠው መድኃኒትና እሬጀንቶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/19
በለሚ ኩራ ከ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 8 እሞራው መታሰቢያ ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት አመት ከዚህ በታች የተቀመጠው መድኃኒትና እሬጀንቶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
ሎት |
የኢቃዉ አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ |
|
1 |
1 |
የህከምና እታ መድኃኒትና ሬጀንቶች |
40,000 |
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብርለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
2. ገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገበ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ቲን ቁጥር ያላቸው፡፡
4. ተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. የገቢዎች ከሊራንስ የጨረታ መሳተፊያ ያለው፡፡
6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 200 ብር በመከፈል የጨረታ ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 48 ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቶች ጨረታው ከወጣበት ቀን እንስቶ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 48 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
8. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ ጠዋት 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ የሚቀጥለውን የስራ ቀን በመጠቀም በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
9. ዘግይቶ የሚመጣ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
10. ተጫራቾች ሲያሸንፉ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
11. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና የሚቀርብባቸውን እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
12. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፋቸውን መድኃኒትና ሬጀንቶች በራሱ ትራንስፖርት የመስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
13. ጤና ጣቢያው ለጨረታ ካቀረበው እቃ 20% ድረስ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
15. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 6ዐ ቀን ነው፡፡
ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማሰራት አለባቸው፡፡ 16.
17. በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ኦርጅናል መሀተም ሊኖር ይገባል፡፡
18. ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ዝርዝር ላይ ቫት ማካተት አለባቸው፡፡
19. ተጫራቾች የተፈለገውን እቃ ሳይሰርዙ ሳይጨምሩና ሳይቀንሱ ለተጠቀሰው መድኃኒት (እሬጀንት ዋጋ ብቻ በዋጋ መሙያ ላይ መሙላት አለባቸው ይህን ያላደረገ ተጫራች ከውድድሩ ይሰረዛል፡፡
20. ከጨረታ ሰነድ ውጭ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
21. የጨረታ መስከበሪያ በ ወረዳ 8 እሞራው መታሰቢያ ጤና ጣቢያ ስም ሲፒኦ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
አድራሻ፡- ወደ ሰሚት በሚወስደው መንገድ ፊጋ መብራቱ ጋር እንደደረሱ ወደ ግራ 30 ሜትር ገባ ብሎ፡፡
ስልክ:-0118593464
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር የመረዳ 8 አሞራው መታሰቢያ ጤና ጣቢያ
