የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(ኢኢግልድ) ለስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 01/2019
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(ኢኢግልድ) ለስራ አገልግሎት የሚውሉ ሎት አንድ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ሎት ሁለት የተለያዩ መጠን ያላቸው የመኪና ጎማዎች ፣ሎት ሶስት የተለያዩ አምፒር ያላቸው የመኪና ባትሪዎች፣ ሎት አራት የተለያዩ የጋራዥ የወርክ ሾፕ መሳሪያዎች (ሎት አምስት የቶርኖ ስራዎች (machine shop) እና ሎት ስድስት የፖምፒስታ ስራዎች (injection pump repair) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፡የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዝርዝር የተመዘገበበት የምስከር ወረቀትና ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ እንዲሳተፍ የተፃፈለትን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡ ለዚህ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለሎት አንድ ብር 500.00(አምስት መቶ ብር)፣ለሎት ሁለት ብር400(አራት መቶ ብር)፣ ለሎት ሶስት ብር 300 (ሶስት መቶ ብር )ለሎት አራት ብር 300(ሶስት መቶ ብር ለሎት አምስት ብር 300 ሶስት መቶ ብር እና ለሎት ስድስት ብር 300(ሶስት መቶ ብር) በመከፈል ከድርጅቱ የጋራዥ አገልግሎት ማዕከል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶች በተለያዩ በሰም በታሸጉ ፖስታዎች በማድረግ እንዲያቀርቡ እያሳሰብን፤ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ በዘኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኢግልድ ዋና መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ከኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች የተለያዩ መጠን ያላቸው የመኪና ጎማዎች ፤የተለያዩ አምፒር ያላቸው የመኪና ባትሪዎች እና የተለያዩ የጋራዥ የወርክ ሾፕ መሳሪያዎች ናሙና (ሳምፕል) ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው:: ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት እንድ ብር 150,000.00 (አንድ መቶ አምሳ ሺህ ብር) ለሎት ሁለት ብር 100,000(አንድ መቶ ሺህ ብር) ለሎት ሶስት ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ ብር)፣ ለሎት አራት ብር 40,000(አርባ ሺህ ብር) እና ለሎት አምስት ብር 50,000(አምሳ ሺህ ብር እና ለሎት ስድስት ብር 40,000(እርባ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise) ስም በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ከጨረታው ቴክኒካል ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ እድራሻ አዲስ አበባ በአራዳ ከፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተ ሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ ወደ ዮሃንስ በሚወስደው መንገድ ጣሊያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ መ/ቤት፣ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ:-በስልክ ቁጥር 0111-26-20-45 በመደወል ወይም በአካል በመጎብኘት ማግኘት ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
