ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ(በቀድሞ ስሙ ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ) ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ሥልጣንና ውክልና መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ(በቀድሞ ስሙ ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ) ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ሥልጣንና ውክልና መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
| የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪውቅርንጫፍ | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የቦታው ስፋት | የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር | የንብረቱ
ዓይነት |
የጨረታው መነሻ ዋጋ /ብር/ | ጨረታ የሚከናወንበት | |||
| ከተማ | ክ/ከተማ | ወረዳ | ቀን | ሰዓት | |||||||
| አቶ አብርሀም መንግስቱ ካብትይመር | ወ/ሮ ነፃነት ፈንታሁን አያሌው | ሜክሲኮ ፕሪሚየም | አዲስ አበባ | ጉለሌ | 10 | 735 ካሬ ሜትር | AA000101002477 | መጋዘን እና G+M+4
(ህንፃ)
|
108,799,193.66 | ነሐሴ 21 2018 ዓ.ም | ከጠዋቱ 4፡00-5:30 |
የጨረታ ደንቦች፡–
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ስም የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) በማስያዝ መመዝገብ ይችላሉ።
- የተጫራቾች ምዝገባ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል። በጨረታው የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም።
- ጨረታው ከላይ በሰንጠረዡ በተገለጸው ቀንና ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ይካሄዳል።
- በጨረታው ላይ ተጫራቾች፣ አስያዥና ተበዳሪ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ት ይካሄዳል፡፡
- የንግድ ማህበራትን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ ፅሁፍ የያዘና በማሀበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ የተገለጸለት ተጫራች ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል። ባይከፍል ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል።
- በንብረት ማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈል ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የሊዝ ክፍያ ወይም ሌላ ማንኛውንም ክፍያ ገዢው ይከፍላል።
- ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
- ለበለጠ ማብራሪያ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ዋናው መሥሪያ ቤት በስልክ ቁጥር 011 5 31 81 17 (የህግ አገልግሎት መምሪያ) ወይም አበዳሪውን ቅርንጫፍ በአካል ቀርቦ ማነጋገርና ንብረቱን የሚጎበኙበት ሁኔታ ማመቻቸት ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
