የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 2 እና ከዚያ በላደ የጠቅላሳ እና የመንገድ ስራ ተቋራጭ (GC/RC-2 and above) ዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀክትን በዲዛይን ግምገማ እና ግንባታ (Design-Build of Unpaved DC-4 Emergency Access Road Construction at Gondar and Gambella Airports Project) የውል ዓይነት በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር SSNT-T626
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 2 እና ከዚያ በላደ የጠቅላሳ እና የመንገድ ስራ ተቋራጭ (GC/RC-2 and above) የሆኑ የሀገር ውስጥ ጨረታ ለመሳትፍ ፈቃድ ያላቸው የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ በጎንደር እና ጋምቤላ አውሮፕላን ማረፌያዎች የDC-4 ያልተነጠፈ የአደጋ ጊዜ መዳረሻ መንገድ ዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀክትን በዲዛይን ግምገማ እና ግንባታ (Design-Build of Unpaved DC-4 Emergency Access Road Construction at Gondar and Gambella Airports Project) የውል ዓይነት በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቶች ፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የታደስ የምዝገባ ምስከርወረቀት ከተፈቀደለት አካል በተጠቀሰው ምድብ ማቅረብ የሚችሉ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (PPPAA) የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር1000006958277 (E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T626 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 / አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ስ150 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ዓርብ, ነሐሴ 15 2018 ዓ.ም እስከ ከረፋዱ 05:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መከፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከረፋዱ በ05:30 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ: የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ እየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517-8025
ኢ.ሜይል: KidistTa@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
