በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በሰቆጣ ከተማ የሚገኘው የዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒዪን ኃ/የተወሰነ ለዩንዪኑ ምርት እና ግብዓት ለማጓጓዝ አገልግሎት የሚውል ሲኖ ካሶኒ 2025 ሞዴል ባለ 400 /አራት መቶ/ የፈረስ ጉልበት የጭነት ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ለሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በሰቆጣ ከተማ የሚገኘው የዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒዪን ኃ/የተወሰነ ለዩንዪኑ ምርት እና ግብዓት ለማጓጓዝ አገልግሎት የሚውል ሲኖ ካሶኒ 2025 ሞዴል ባለ 400 /አራት መቶ የፈረስ ጉልበት የጭነት ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉትን የተገስፁት መስፈርቶች የሚያሟሱ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. በዘመኑ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብርን የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና (የምትችል) ከሚገዛው የጭነት ተሽከርካሪ አገልግሎት ጋር የተዛመደ ንግድ ሥራ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት (Value Added Tax Certificate)ተመዝጋቢ ከሆኑ /የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (Tax Payer ldentificain Number) እንዲሁም ሌሎች ለጨረታው የሚጠቅሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል (የምትችል)
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሰቆጣ ከተማ በሚገኘው ዩንየኑ ዋና ቢሮ 1 የኢትዮጵያ ብር 250 /ሁለት መቶ አምሳ ብር ብቻ/ በመከፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።
3. የጨረታ ተሳታፊዎች የመሸጫ ዋጋቸውን በሰንጠረዥ በተገለፅው ዝርዘር ሁኔታ መሠረት መሙላት አለባቸው።
4. የጨረታ ዋጋውን ከመግለፅ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ተጫራቶች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው በታወቁ ባንኮች ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ /ዋናውን የገቢ ደረሰኝ /ከማወዳደሪያ ሃሳብ ጋር አብሮ ማስገባት ሲኖርባቸው በጨረታ ሰነዱ ከተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም።
5. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት አይቻልም።
6. በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለሳል።
7. የጨረታ ሰነዱን ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚጀምረው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ ለከታታይ 10/አስር የስራ ቀናት/ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት ዋቢ ሁለገብ /የገ/ኅ/ስ/ማ ኃላፊነቱ የተወሰነ ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ በ11 /አስራ አንደኛው/ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽገው ከጠዋቱ 3፡30 ጨረታው ይከፈታል በጨረታ መክፈቻ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ አከፋፈት ባይገኙም በጨረታ አከፋፈት ሥርዓቱ ተገዥ ይሆናሉ።
9. አሽናፊው እንደታወቀም አሽናፊው ያሽነፈበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ ለውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ5 አምስት ቀናት ውል መያዝ አለበት ይህ ካልሆነ ግንዩንየኑ የጨረታ ማስከበሪያውን 2% በመውረስ የራሱን አማራጭ ይወስዳል፡፡
10.ተጫራቾች ከጨረታው ጋር በተያያዘ እና ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎች በተዘጋጀው የተጫራቾችመመሪያ መሰረት ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
11.ዩንየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
12. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ዋቢ ሁለገብ የገ/ኅ/ሥ/ማኅበር ኃላፊነት የተወሰነ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0334401173/0941821789/0933214815/0968945900 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኀራት ዩኒየን ኃ/የተወሰነ
