Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል
  • Address ከሚሴ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 51 99 99 75
  • Website
  • Deadline10 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineAdiss zemen
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2026-08-10 10:30:00
  • Categories Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

በአብከመ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ የሲቲእስካን እና ራጅ ከፍል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በጡም ለማሰራት ይፈልጋል፡፡


የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ


በአብከመ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ የሲቲ እስካን እና ራጅ ከፍል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በጡም ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ፡-

1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፤የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ ለስራው የምዝገባ የምስከርወረቀት ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ /TIN/ ያላቸው፡፡
2. የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 50 በግዥ/ፋ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዘውትር በስራ ቀንና ሰዓት ለሰነድ የማይመለስ የኢትዮ. ብር 300/ሶስት መቶ ብር ብቻ /በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናና ኮፒ በማድረግ በታሽገ ኤንቨሎፕ _ በአብክመ ከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ ስድስተኛው/16/ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ግዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 4፡01 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ይታሽጓል፡፡
4. ጨረታው በአስራ ስድስተኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመከፈቻ እለቱ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
5. ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% /ከሁለት ፐርሰንት/በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ ትእዛዝ/CPO/ማስያዝ አለባቸው ::
6. የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ግዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምርዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8. የስራው ቦታ በከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ይሆናል፡፡
9. ውድድሩ በጠቅላላ ዋጋ የምንወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
10. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር0972847872 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡


በአብክመ ጤና ቢሮ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል

Save Tender