በደቡብ/ኢ/ከ/መ/ በወላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ/ኢ/ከ/መ/ በወላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር የተለያዩ ዓይነት ጥራታቸውን የጠበቁ፡ ኦርጅናል ዕቃዎችን በከተማ አስተዳደሩ ስር ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች 1ኛ. የጽ/መሣሪያ 2ኛ፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ 3ኛ. ሞተር ሳይክል 4ኛ.የህንፃ መሣሪያ መሣሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
1. ተጫራቾች አግባብነት ያለውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ ም/ወረቀት፣የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር/ቲን/ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ምዝገባ ሰርተፍኬትና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
2. ለሚያቀርቡት _ አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክበተመሰከረለት ቼክ/CPO/የባንከ ጋራንቲ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፣
3. ጨረታውን አሸናፊ የሆነ ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን 10% ቼከ/CPO/ ካሽ ወይም ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት!
4. ተጫራቾች በየሎቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ ወደ ቦዲቲ ከተማ ገቢዎች ባለሥልጣን ቅ/ጽ/ቤት ድረስ በአካል ቀርበው በመክፈል ሰነዱን ከቦዲቲ ከተማ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ኦርጅናል ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሰነዱ ገብቶ ከተጠናቀቀ በኋላ በዕለቱ በ4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
6. ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት / የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
7. የተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቦታው ላይ አለመገኘት ጨረታውን አያስተጓጉለውም፣
8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፏቸውን ዕቃዎች ቦዲቲ ከተማ ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ኬዝ ቲምና ንብረት አስተዳደር ከፍል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ከቫት ጋር ወይም ያለቫት መሆኑን መግለጽ አለባቸው ካልተገለጸ የቀረበው ዋጋ ከቫት ጋር እንደሆነ ይወሰዳል፡፡
11. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ናሙና አስቀድመው ማቅረብ አለባቸው፣
12. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ወይም ሰንበት ከሆነ ለቀጣይ የሥራ ቀን በማስታወቂያው በተጠቀሰው ሰዓትና ጊዜ ይከናወናል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር 0465590336 /0465590296 መጠቀም ይችላሉ
በወላይታ ዞን የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ፋ/ ጽ/ ቤት
