ተስፋ ለሕፃናት ድርጅት የሚገኙ ያገለገሉ ልዩ ልዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችንና፥ ለመለዋወጫ የሚያገለግል አንድ ሞተር ሳይክል ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ያገስገሱ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች የጨረታ ማስታወቂያ
ተስፋ ለሕፃናት ድርጅት በኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አዋጅ ቁጥር 1113/2019 ዳግም ተመዝግቦ በልዩ ልዩ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ የማህበረሰብ ክፍሎችን የድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎት በመስጠት፣ እንዲሁም በማህበረሰብ ልማት ላይ የተለያዩ ፕሮጀከቶችን በመተግበር ላይ የሚገኝ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፣በሐረርከተማ በሚገኘው የምስራቅ ማስተባበሪያ ቢሮአችን ውስጥ የሚገኙ ያገለገሉ ልዩ ልዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችንና፥ ለመለዋወጫ የሚያገለግል አንድ ሞተር ሳይክል ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው
1. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) እየከፈሉ ሐረር ከተማ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው መዶብ ቢዝነስ ሴንተር 2ኛ ፎቅ በቅርንጫፍ ቢሮአችን በመምጣት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክበተረጋገጠ ሲፒኦ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡ አሽናፊ ለሆኑት የጨረታ ማስከበሪያው በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ የሚታሰብ ይሆናል፡፡ ለተሸነፉት ተጫራቾች የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ ሲፒኦ ወዲያው ተመላሽ ይደረጋል።
3. ተጫራቾች አሽናፊ መሆናቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉበትን ዋጋ በ5 ቀናት ከፍለው በ5 ቀን ውስጥ ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣ ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
4. ተጫራቾች ስለ ንብረት አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
5. ጨረታው ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 5፡30 ላይተጫራቾች/ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
6. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0111222621/0916891300 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
7. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ተስፋ ስሕፃናት ድርጅት
