Tender Detail

Tender Details


የዶዶታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በወረዳዉ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ኤሌክትሮክስ፣የጽህፈት መሣሪያዎች፣የቢሮ ዉስጥ ልዩ ልዩ አላቂ ዕቃዎች፣የጽዳት ዕቃዎች፣የመኪና ጎማዎች እና የሠራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01/2019

 

የዶዶታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በወረዳዉ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ኤሌክትሮክስ፣የጽህፈት መሣሪያዎች፣የቢሮ ዉስጥ ልዩ ልዩ አላቂ ዕቃዎች፣የጽዳት ዕቃዎች፣የመኪና ጎማዎች እና የሠራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

1.      ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ  ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax payer registration number) ያላቸው እና በፌዴራል፣ በክልል፣ በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የተሞላውን የጨረታ ሰነድ ዋናውና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

2.      ተጫራቾች ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮክስ፣ የጽፈት መሣሪያዎች፣ የቢሮ ዉስጥ ልዩ ልዩ አላቂ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች እና የሠራተኞች ደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በጽህፈት ቤቱ ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000039238695 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በጽህፈት ቤቱ የግዢና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 ድረስ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

3.      ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4.      በቀጣይ እለት ማለትም በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ የግዢና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 ይከፈታል።

5.      የመክፈቻው እለት በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተራ ቁጥር 4 በተጠቀሰዉ መሰረት ጨረታው ይከፈታ።

6.      ማንኛዉም ተጫራች ለእያንደንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000 (አስር) በአቅራቢያቸው በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ (C.PO) ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል።

7.      አሸናፊው ተጫራች ያለ ምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ አስፈላጊ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና ዕቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ዴራ ከተማ ውስጥ በሚገኘዉ የወረዳዉ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርበታል።

8.      ማንኛውም ተጫራች እስክርቢቶዎች፣ የፕሪንተር ቀለሞች እና ደንብ ልብስ ላይ የሚወዳደር ለሚወዳደርበት እቃ ናሙና (sample) ማቅረብ አለበት።

9.      ተጫራቹ አሸናፊ ከሆነ ላሸነፈበት ዕቃ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መግባት ይጠበቅበታል። ዶዶታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አርሲ ዴራ ከተማ ከአዳማ በአሰላ መስመር 25 ኪ.ሜ

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር (09 12 31 13 09) (09 10 37 94 35) (09 10 02 21 23 ይጠይቁ።

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአርሲ ዞን የዶዶታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Dodota District Finance Office (Arsi Zone, Oromia) is procuring permanent office furniture, electronics, stationery materials, office consumables, cleaning supplies, vehicle tires, and staff uniforms for sector offices for the 2019 budget year. Bids close at 4:00 and open at 4:30 on the 16th working day from the announcement date (posted 2026-08-04). The non-refundable bid document costs 500 ETB, and a 10,000 ETB bid bond is required by C.P.O. only. Bidders need a valid renewed trade license, VAT registration, taxpayer number, and supplier registration certificate; samples are required for stationery items, printer inks, and uniforms, and delivery is to Dera town at the bidder's own transport cost.
Save Tender