Tender Detail

Tender Details

  • Company የኦሮሚያ ስቴት ዩንቨርስቲ ጅማ ካምፓስ
  • Address , Phone: 0911748607
  • Website
  • Deadline19 Aug 2026, 11:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price300 (ሦስት መቶ)
  • opening dateጨረታው አየር ላይ ለተከታታይ16 ቀን ቆይቶ በ16 ኛው ቀን 05፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • Categories Catering And Cafeteria Services

የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርስቲ በሐሮ ደንበል ዳር ያለውን የዩኒቨርስቲውን ካፍቴርያ በማከራየት ለዩኒቨርስቲው ሰራተኞች፣ ለአከባቢው ማህበረሰብ እና ለተለያዩ ስልጠና የሚመጡ ሰልጣኞች ወይም እንግዶች የካፌ እና ሬስቶራንት አገልግሎት ለማቅረብ በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላችውን ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርስቲ በሐሮ ደንበል ዳር ያለውን የዩኒቨርስቲውን ካፍቴርያ በማከራየት ለዩኒቨርስቲው ሰራተኞች፣ለአከባቢው ማህበረሰብ እና ለተለያዩ ስልጠና የሚመጡ ሰልጣኞች ወይም እንግዶች የካፌ እና ሬስቶራንት አገልግሎት ለማቅረብ በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላችውን ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1.    የዘመኑን 2018 ዓ.ም ግብር የከፈሉበትን ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል።

2.    ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር የያዘውን ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ) በመክፈል ባቱ በሚገኝው የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርስቲ በስራ ቀንና ሰዓት ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ባቱ/ዝዋይ/ ከተማ በዩኒቨርሲቲው ግዥ ቢሮ ቁጥር TR-012 እና አዲስ አበባ ላንቻ ክርስቲና ፕላዛ ሕንጻ 4ኛ ፎቅ በአካል በመቅረብ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።

3.    ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በማያያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቭሎፐ አድርገው ጨረታውን ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 5፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4.    ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ተከታታይ የስራ ቀናት በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ታሽጎ በ5፡30 ሰዓት ባቱ ከተማ በዩኒቨርስቲው ግዥ ቢሮ ቁጥር TR –012 ይከፈታል።

5.    ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በካለንደር የሚዘጉ የበዓላት ቀን ወይም የእረፍት ቀን ቢሆን የጨረታው መክፈቻ ቀን በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል።

6.    ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚያስረክቡበትን ድምር ዋጋ 2% (ሁለት ፐርሰንት) ጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፕኦ(CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

7.    አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን የኪራይ ዋጋ የውል መስከበሪያ 10%(አሥር ፐርሰንት) በባንክ በተረጋገጠ ሲፕኦ(CPO) በማሰያዝ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ውል ይፈራረማሉ።

8.    ለተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ያስያዙት ሲፕኦ (CPO) የጨረታ ሰነድ ተመርምሮ አሸናፊ ተጫራች እንደታወቀ ይመለስላቸዋል።

9.    ዩኒቨርሲቲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-046-141-21-56 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

 

የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርስቲ

✨ messages.ai_summary
- Oromia State University (Jimma Campus) is tendering the lease of its cafeteria at Haro Dembel for cafe and restaurant services to university staff, the local community, and trainees or guests. - Eligible bidders must have a valid renewed business license for the current 2018 E.C. year with tax paid. - Bid documents cost a non-refundable 300 ETB and are available during the first 15 consecutive working days. - Bids must be submitted by 5:00 on the 16th consecutive working day; opening is at 5:30 the same day. - A 2% bid security in the form of a bank-guaranteed CPO is required, and the winner must provide a 10% contract performance security.
Save Tender