የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የክለቡን 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አስመልክቶ በተለያዩ ዝግጅቶች ማክበር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዝግጅቶች የመስራት ልምድ ያላችሁ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የክለቡን 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አስመልክቶ በተለያዩ ዝግጅቶች ማክበር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዝግጅቶች የመስራት ልምድ ያላችሁ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ ስለሆነም ሊሰሩ የታሰቡ ዝግጅቶች
- የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ዓመታዊ የደጋፊዎች ሩጫን በአዲስ አበባ ከተማ ማካሄድ
- የክለቡን 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አስመልክቶ በተመረጡ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የእግር ኳስ ውድድር ማድረግ
- የሙዚቃ ኮንሰርት ማድረግ
- የፓናል ውይይት ማካሄድ ሲሆኑ
ስለሆነም እነዚህን ዝግጅቶች ለመስራት ከዚህ በታች የጠቀስናቸውን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ቲን ሰርተፊኬት
- ከዚህ በፊት በኢቨንት ኦርጋናይዘር ሙያ መስራታችሁን የሚያረጋግጥ የመልካም ስራ ማጠናቀቂያ ምስክር ወረቀት
- ከላይ የተጠቀሱትን ዝግጅቶች ልትሰሩ የምትችሉበትን ዋጋ
- የብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ጨምሮ በማቅረብ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የጨረታ ሰነዱንም ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሰባት የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በመክፈል በክለቡ ፅ/ቤት ቡናና ሻይ ህንጻ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 114 የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ እስከ ነሀሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ቀን 10፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ዓለማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ዋጋቸውን ሞልተው ማስገባት አለባቸው፡፡
- ክለቡ የተሻለ አማራጭ ካገኙ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ዝግጅቶቹን ሊሰሩበት የሚችሉትን ዋጋ ሲሞሉ ቫትን ጨምሮ መሆን ይኖርበታል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911 48 10 72 በስራ ሰዓት ደወለው መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ
