የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 የመንገድ /ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን (Category-1 Road/General Construction) በጨረታ አወዳድሮ በ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለሁለቱም መንደርደሪያ ሜዳዎች የአደጋ ጊዜ መዳረሻ መንገዶችን እና ለ 07L/25R የመንደርደሪያ ሜዳ ጫፍ የደህንነት ስፍራ ዲዛይን እና ግንባታ(Design Build of Emergency Acc
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: -SSNT-T635
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 የመንገድ /ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን (Category-1 Road/General Construction) በጨረታ አወዳድሮ በ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለሁለቱም መንደርደሪያ ሜዳዎች የአደጋ ጊዜ መዳረሻ መንገዶችን እና ለ 07L/25R የመንደርደሪያ ሜዳ ጫፍ የደህንነት ስፍራ ዲዛይን እና ግንባታ(Design Build of Emergency Access Roads on Both Sides of Runways 07L/25R and 07R/25L, Including Runway 07L/25R RESA at AABIA) ለማሰራት ይፈልጋል::
ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የታደሰ የምዝገባ ምስከርወረቀት፣ ከተፈቀደለት አካል በምድብ R/GC-1 ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (PPPAA) የአቅራቢነት የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ የፕሮጀከቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ በ180 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 3፣ 2018 ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ሁለት መቶ ብር (200.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T635 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ሁለት መቶ ሺህ ብር (200,000.00ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ መቶ ሃምሳ ቀናት (150) ቀናት የሚቆይ ይሆናል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በተለያየ ኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ጳጉሜ 3፣ 2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 5:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ:-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ከፍል
ስልክ ቁጥር Tel: +251 115 17 4028/8025
ኢ-ሜይል: AynalemAy@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
