የሀዋሳ ላይ ከተማ ስፖርት ክለብ በ2019 ዓ/ም ለክለቡ ስፓርተኞችና ኮች ስታፍ የስፖርት ትጥቅ ግዢ ለመፈፀም በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ላይ ከተማ ስፖርት ክለብ በ2019 ዓ/ም ለክለቡ ስፓርተኞችና ኮች ስታፍ የስፖርት ትጥቅ ግዢ ለመፈፀም በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት፤-
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ።
1. በሥራ መስኩ ሕጋዊ የታደሠ ንግድ ፍቃድ፤የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ
3. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች ለተመዘገቡ ጨረታዎች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ (የምስክር) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቀረብ ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ ስፖርት ከለብ ቢሮ በመቀረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 3,000.00/ ሶስት ሺህ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
6. የጨረታ ሠነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኢንቨሎፕ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም በሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ ፋይናንስ ቢሮ አርተፍሻል ሜዳ ቢሮ ቁጥር 1 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. በጨረታ ሰነድ ላይ ለሚጠየቁ ዕቃዎች ናሙና የጨረታው ሠነድ በሚገባ ቀን ለእያንዳንዱ ዕቃዎች ላይ ኮድ የድርጅቱን ማህተም/ በማስቀመጥ በጨረታው አከፋፈት ሥነሥርዓት ላይ መቅረብ አለባቸው።
8. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜ እሁድ ከሆነ እንዲሁም የበዓላት ቀን ከሆነ በተመሣሣይ ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
9. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ ተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡-046-212-4176
የሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ
