ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተየግ ኩባንያ የተለያዩ ኤሌክትሪክ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር
ECA/038/2018
1. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተየግ ኩባንያ የተለያዩ ኤሌክትሪክ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ከግዥው ጋር አግባብነት ያለው የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልፅ ወቅታዊ ደብዳቤ (Tax Clearance)፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ፣ ቲን ሰርተፍኬት እና ቫት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሀምሌ 30 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ እስከ ነሀሴ 08/2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2:30-6:30 እና ከሰዓት በኃላ ከ7:30-11:00 ድረስ እንዲሁም ቅዳሜ እስከ 6:30 ድረስ ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴይሪ ጀርባ ከኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው ኢትዮ አግሪ ሴፍት ህንፃ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የምትወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት በስም በታሸገ ፖስታ/Envelop/ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከሀምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ነሀሴ 08/2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን ነሀሴ 08/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ይከፈታል።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት፡-
ü አንድ ዋና /Original የመጫረቻ ሰነድ ለብቻው በታሸገ ፖስታ
ü አንድ ቅጂ /Copy/ የመጫረቻ ሰነድ ለብቻው በታሸገ ፖስታ
ü ሁሉንም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት
ü በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል
ü ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፤ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች ለሚገዛው ዕቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ / CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ. የተ.የግል ማህበር በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ከላይ የተገለፀውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታ የሚሰረዙ መሆኑን እንገልፃለን።
6. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-667 6204 ፋክስ ቁጥር 011-673 2006 መጠቀም ይችላሉ።
7. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ. የተ.የግል ማህበር ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ. የተ.የግል ማህበር
