Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/
  • Address Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 098288 2826
  • Website
  • Deadline15 Aug 2026, 5:30 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price
  • opening dateበጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት
  • Categories Ict Equipment'S And Its Accessories , Office And Home Furniture

የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች ግዢ


የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች ግዢ የጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/ እና ፔስታሎዚ የህፃናት መርጃ ድርጅት /PCF/ በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ 16 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ "በ16 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል" የሚል ሙሉ ትኩረቱን በትምህርት ጥራት ላይ ያደረገ ፕሮጀከት በመተግበር ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም ድርጅታችን ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት / ECD/ ለእነዚህ አጋር ትምህርት ቤቶች የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) እና የዲጂታል ትምህርትን (Digital Education) ለማሻሻል እና ተማሪዎችን እና መምህራንን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚውሉ ግብዓቶችን ለመግዛት አቅዷል። በመሆኑም የሚከተሉትን የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች ለማቅረብ የምትፈልጉ እና መስፈርቶቹን የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። የሚገዙት ቁሳቁሶችም የሚከተሉት ናቸው።

ሎትዘርፍዝርዝር መረጃምርመራ
1.ኮምፒውተር እና ተያያዥ ቁሳቁሶችዝርዝር መረጃውን በጨረታው ሰነድ ውስጥ ያገኙታል
2.ወንበር እና ጠረጴዛዝርዝር መረጃውን በጨረታው ሰነድ ውስጥ ያገኙታል

ተጫራቾች ማወቅ እና ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች:-

  1. ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና በዘርፉ ለመስራት የሚያስችላቸው ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የቲን ሰርተፊኬት እና የቫት ሰርተፊኬቱን ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ የሚጠቀሙ ከሆነ በብርሃንና ሰላም የታተመ የኪው አር ኮድ ያለው ደረሰኝ የሚያቀርቡ፣
  4. ያሸነፉበትን እቃዎች በራሳቸው ትራንሰፖርት አጓጉዘው ድርጅቱ ወደሚያዘጋጀው ስቶር ማድረስ የሚችሉ፣
  5. ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች የጽሁፍ ዋስትና መስጠት የሚችሉ፣
  6. ቁሳቁሶቹን በተቀመጠው ስፔሲፊኬሽን መሠረት ማቅረብ የሚችሉ እና በድርጅታችን ባለሙያ የቴክኒክ ፍተሻ ካለፉ ብቻ የምንቀበል መሆኑ እንዲታወቅ፣
  7. የጨረታ ማስከበሪያ የ 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር CPO በኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት ስም አሰርቶ ከጨረታ ሰንዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከድርጅታችን የጨረታ ሰነዱን በነጻ በመውሰድ ቁሳቁሶቹን የምታቀርቡበትን ዋጋ በታሸገ ጫንቨሎፕ ማስገባትና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ግድራሻ፦ አዲስ አበባ፣ ቦሌ አለም ህንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልክ: 0982 88 2826

ማሳሰቢያ፦

  1. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ግብዓት ከማቅረባቸው በፊት ሳምፕል ማሳየት ይኖርባችኋል።
  2. ተጫራቾች የምታቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ማሳየት ይኖርባችኋል። በትክክል ካልተገለጸ ቫት እንደተካተተ ተደርጎ ይቆጠራል።
  3. ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ያለ ምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ማስታወቂያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት /ECD/

✨ messages.ai_summary
- Procurement of technology equipment, including ICT and digital education resources, for 16 primary schools in Addis Ababa, under the project “Improving student outcomes in 16 primary schools.” - Issued by the Ethiopian Center for Development (ECD) jointly with Pestalozzi Children’s Foundation (PCF); items are divided into Lot 1: computers and related accessories, and Lot 2: chairs and tables. - Posted on 2026-08-12; bids must be submitted within 5 consecutive working days from the newspaper announcement date. - Bid bond: 20,000 ETB CPO in the name of the Ethiopian Center for Development. - Key requirements: renewed trade license, TIN and VAT certificates, written warranty for electronic devices, delivery by the bidder’s own transport to the organization’s store, sample submission for winning bidders, and clear indication of whether VAT is included in the price.
Save Tender