ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች (መኪናዎች፣ ትራክተር፣ ተጎታች ጋሪዎች፣ ሞተር ሳይክሎች እና ብስክሌቶች) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች (መኪናዎች፣ ትራክተር፣ ተጎታች ጋሪዎች፣ ሞተር ሳይክሎች እና ብስክሌቶች) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡-
- ሎት-1 መኪናዎች
- ሎት-2 ትራክተር
- ሎት-3 ተጎታች ጋሪዎች
- ሎት-4 ሞተር ሳይክሎች
- ሎት-5 ብስክሌቶች
- ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት አድራሻ ሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ እና ሀዲያ ዞን ጤና መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
- በተሽከርካሪዎች ጨረታ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም እና የተጫራቾች መመሪያ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በተከታታይ በ10/አስር/ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በተናጠል፡- ሎት-1 መኪና ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/፣ ሎት-2 ትራክተር ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/፣ ሎት-3 ተጎታች ጋሪ ብር 400.00/አራት መቶ ብር/፣ ሎት-4 ሞተር ሳይክል ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ እና ሎት-5 ብስክሌቶች ብር 400.00/አራት መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመከፈል ከሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 17 በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩትን ተሽከርካሪ/ዎች በሎት በተናጠል ወይም በድምር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመነሻ ዋጋ 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ/CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ መሙያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20/ሃያ/ ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታ አንድ ዋና/Original/ እና ቅጂ/Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በፖስታ ታሽጎና እንደገና ሁለቱም በአንድ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 17 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሃዝና በፊደል በመጻፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለባቸው ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች ለመግዛት የፈለጉትን ተሽከርካሪ/ዎች የጨረታ ዋስትና ካስያዙት ተሽከርካሪ/ዎች ውጪ መወዳደር አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ከአንድ በላይ ተሽከርካሪዎች (መኪና፣ ትራክተር፣ ተጎታች ጋሪዎች፣ ሞተር ሳይክሎች እና ብስክሌቶች) መጫረት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ21ኛው/ሃያ አንደኛው ቀን ከጧቱ 4፡30 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ5፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪዎች (መኪናዎች፣ ትራክተር፣ ተጎታች ጋሪዎች፣ ሞተር ሳይክሎች እና ብስክሌቶች) አሸናፊነታቸው በደብዳቤ በተገለጸ በ10/አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው ሆኖም በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ገዢው ካላነሳ ለሚደርሰው ለማንኛውም ችግር ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪዎች (መኪናዎች፣ ትራክተር፣ ተጎታች ጋሪዎች፣ ሞተር ሳይክሎች እና ብስክሌቶች) ከመንግስት የሚፈለግ ግብርና ቀረጥ በሻጩ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የተሽከርካሪ ስም ማዘዋወሪያ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች በሙሉ በአሸናፊው ይሸፈናል፡፡
- ተጫራቾች የመነሻ ዋጋ እና የዋጋ ማቅረቢያ የጨረታ ሰነድ አካል ሲሆን ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046-555-2337/2316 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
✨ messages.ai_summary
- Used vehicles (cars, tractors, trailers, motorcycles, and bicycles) will be sold as-is through an open public tender.
- Issued by the Hadiya Zone Finance Department, Central Ethiopia Regional Government.
- Submission deadline is on the 21st day at 4:30 AM, with bid opening at 5:00 AM the same day.
- Bid document prices (non-refundable): Lot 1 cars 500 ETB, Lot 2 tractors 500 ETB, Lot 3 trailers 400 ETB, Lot 4 motorcycles 100 ETB, Lot 5 bicycles 400 ETB. Bid bond: 20% of the starting price, only via bank-confirmed CPO.
- Any Ethiopian individual or organization may participate. Vehicles are located at the Hadiya Zone Finance Department and Hadiya Zone Health Department compounds.
