Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
  • Address በምስራቅ ሸዋ ዞን ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462 -114-616
  • Website
  • Deadline25 Aug 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 500 /አምስት መቶ/
  • opening dateበ16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኋላከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Categories Building Materials

የተፈጩ ጠጠሮች ግዥ


የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ኢመአ/ሻሽ/002/2019

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ለ2019 በጀት ዓመት ለዲስትሪከቱ የመንገድ ጥገናና ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው የተፈጩ ጠጠሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ የምዝገባ ምስከር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ ምስከር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ለ2017 በጀት ዓመት ግብር ስለመከፈላቸው የሚገልጽ ከሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 50, 000.00(ሃምሳ ሺህ /በባንከ በተረጋገጠ ሲፒአ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
  4. ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን ፋይናንሻልና ቴከኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በእለቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
  5. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ በእለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ የሂሳብ ቁጥር 1000002579859 ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ዕቃ ግዥ አ/ን አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይቻላል፡፡
  7. በጨረታው መከፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 0462-114-616 መጠቀም ይችላሉ፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት

✨ messages.ai_summary
- Procurement: Crushed stones of various sizes for road maintenance and construction works. - Issuer: Ethiopian Roads Administration, Shashemene Road Maintenance District. - Dates: Posted on 2026-08-12; bids close on the 16th working day after publication in Addis Zemen newspaper at 8:00 PM and open at 8:30 PM the same day. - Participation costs: Bid document price is 500 ETB (non-refundable); bid bond is 50,000 ETB, accepted only as a bank-confirmed CPO. - Key requirements: Submit renewed 2018 E.C. business license registration, VAT certificate, tax payer registration copy, and clearance for 2017 budget year tax payment; provide one original and two copies of priced financial and technical documents in separate sealed envelopes.
Save Tender