የተለያዩ እቃዎች ግዥ (የመኪና ና የማሽነሪ መለዋወጫ እና ጎማና ባትሪ)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማ ና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት በ 2019 በጀት ዓመት ለጽቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ በሎት አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል ፡፡
ስለዚህ -
- ሎት 1- የመኪና ና የማሽነሪ መለዋወጫ (ስፔርፓርት) እቃዎች
- ሎት 2 - የማሽነሪ እና የመኪናዎች ጎማና ባትሪ
ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባቸው -
- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው
- ቲን ነምበር ያላቸው
- የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ(VAT) ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናቶች በመንግስት የስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በብር 100 /አንድ መቶ ብር/መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ - ማስከበሪያ ለሚጫረቱበት ጨረታ በየሎቱ በእያንዳንዱ ማለትም ለሎት1- የማሽነሪና መኪና መለዋወጫዎች ስፔርፓርት ግዥ 30,000 ብር ለሎት2 ጎማና ባትሪ ግዥ 20,000 ብር ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ በመሂ 1 የተቆረጠ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በባንክ ተረጋገጠ ሌተርኦፍ ከሬዲት ሆኖ መረጃውን ፖስታው ውስጥ አስገብተው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 13 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመ ጊዜ ጀምሮ በ16ኛ ቀን ከቀኑ 4፡00 ስዓት ድረስ ወይም ከዚያ በፊት አንድ ኦርጅናል ና አንድ ፎቶ ኮፒ በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጊዜ ለ40 የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
- ጨረታዉ ቢሮ ቁጥር 13 በተገለጸዉ ቦታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመ ጊዜ ጀምሮ በ16ኛ ቀን ከቀኑ 4፡00 ስዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ወይም ባይገኙ ከቀኑ በ4፡30 ስዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዕቃ ዓይነት ዝርዝር ከሚገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዕቃ ዝርዝር መረዳት ይችላሉ::
- አሽናፊው ድርጅት ንብረቱን ደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማ ና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን በሚሞሉበት ሰዓት ስርዝ ድልዝ መኖር የለለበት ሲሆን የእቃው ናሙና ቢሮ ቁጥር 13 በግንባር በመቅረብ ማየት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ሙሉ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን በሙሉ አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በሎት ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ሙሉ በሙሉ በሞላ ስለሆነ ከመጫረቻ የዋጋ መሙያ ሰነዱ ላይ ክፍት ማድረግ የለባችሁም፡፡ በተጨማሪም የዕቃዎች ብዛት ከበጀት አንፃርሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥራችን 058 1170033 ወይም 0581171208 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ሁሉም ዕቃዎች ጥራቱን የጠበቀና በተጠየቀው ሞዴል መሰረት ኦርጅናል መሆን አለባቸው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያዎች መረጃዎች ካሉ በቢሮአችን በውስጥ ሰሌዳ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት ፅ/ቤት
✨ messages.ai_summary
- The Debark City Administration Urban and Infrastructure Development Office is procuring various items through open tender in two lots: Lot 1 – vehicle and machinery spare parts; Lot 2 – machinery and vehicle tires and batteries.
- Bid documents are available for 100 ETB for 15 consecutive days from publication in the Addis Zemen newspaper. Submission closes by 4:00 PM on the 16th day; opening takes place at 4:30 PM the same day, moving to the next working day if the 16th day is not a working day.
- Bid security: 30,000 ETB for Lot 1 and 20,000 ETB for Lot 2, in the form of a bank-confirmed CPO, cash deposit at the office, an unconditional bank guarantee, or a bank-confirmed letter of credit in ETB.
- Bidders must hold a valid renewed business license and TIN number; VAT registration is required if the procurement amount is 200,000 ETB or above. Bid validity must be 40 working days, and all items must be original and match the requested model.
