Tender Detail

Tender Details

  • Company በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 0222369094
  • Website
  • Deadline20 Aug 2026, 10:45 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceBirr 100 (non-refundable)
  • opening dateበዚሁ ዕለት ከረፋዱ 5፡00
  • Categories Other , Disposal Sale

Sale of Abandoned Goods by Tender


የተተው ዕቃዎች ግልጽ ጨረታ ቁጥር ግ-04/2019 ጨረታ

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 ከቀነ ገደቡ በላይ በመጋዘን በመቆየታቸው ምክንያት እንዲሁም የተተው ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 9 መሠረት የተተው ንብረቶችን GALVANZED STEEL SIRIPS 2 SIDE COATED ART PAPER: LUX ROUND OVEN MEN BRAND SHOES, MEN TROUSER, SHITY MATERIAL, VACUUM FLASK, ALUMINIUM, HAIR CLIPPER, BEDSHEET: PERFUME AND OTHERS እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ መግለጫ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመከፈል ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳቦች ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፤ አዳማ እና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት፡፡ ተሳታፊዎች ዋጋ መሙላት የሚችሉት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተዘጋጅቶ ማህተም ያረፈበት ሠነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አስቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡ በጨረታ ተሽጦ የተወሰደ እቃ ተመላሽ አይደረግም፣ ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም፡፡
  5. የግልጽ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃዎች ለመግዛት የሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ፤ የሞሉበት ሠነድ፤ በተራ ቁጥር 2 የተገለፁትን ማስረጃዎች ኮፒ እና ያቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO በኤንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት እስከ የመጨረሻው ቀን ጠዋት 4፡45 ድረስ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል፡፡ የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
  6. የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበት ቀንን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡45 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 5፡00 ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  7. ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፣ በጨረታ ሽያጭ ውድድር ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም እና የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  8. የግልጽ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት፡፡ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል፡፡
  9. በተራ ቁጥር 8 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ/ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል፡፡
  10. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል፡፡
  11. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ የአቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው፡፡ በጨረታ ተሽጦ በጨረታ አሸናፊው የተወሰደ እቃ አይመለስም፡፡
  12. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-90-94 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Sale of abandoned goods by tender: galvanized steel strips, coated art paper, shoes, trousers, clothing material, vacuum flasks, aluminium, hair clippers, bedsheets, perfume, and other items. Bidders need a valid trade license, tax ID, and proof of tax payment; VAT registration required for items over 500,000 birr.
Save Tender