የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ሁለት አውቶሞቢል ዲዛየር መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ፍላሚንጎ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ሁለት አውቶሞቢል ዲዛየር መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብቻ ጥሬ ገንዘብ በመክፈል ሰነዱን አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ፍላሚንጎ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ህንጻ ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302 ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ትችላላችሁ።
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር የከፈለ።
- በዘርፉ የተሰማሩበት ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።
- አቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ ማስፈርና መጨረሻ ቦታ ላይ ፊርማና ማህተም በመምታት አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 አስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 5,000.00 (አምስት ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከመወዳደሪያ ፖስታ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከሰዓት በኋላ 7፡15 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴያትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ፍላሚንጎ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302 ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 11 92 45 97
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Theater Houses Administration seeks to lease two automobile designer vehicles for its new Children and Youth Theater and Cinema Complex via open tender. Bidders must hold a renewed trade license, sector permit, supplier registration, and VAT certificate.
