የተለያዩ ዕቃዎች (ፌሮ ብረቶች፣ ሴራሚኮች፣ ጎማዎች፣ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የውሃ ዕቃዎች የሻወርና የመፀዳጃ ቤት ዕቃዎች እና ሌሎችም ተዛማጅ ዕቃዎች) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ
ዕቃዎችን ስመሸጥ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ ጋምቤሳ/ስተአ/003/2018
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዝን የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (ፌሮ ብረቶች፣ ሴራሚኮች፣ ጎማዎች፣ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የውሃ ዕቃዎች የሻወርና የመፀዳጃ ቤት ዕቃዎች እና ሌሎችም ተዛማጅ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቶች፡-
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጋምቤላ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ክፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ከነሐሴ 05/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት /Refugee and Returnee Service/ በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራጭ ከነሐሴ 05/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል፡፡ ቅዳሜና እሁድ የስራ ቀናት አይደሉም፡፡
- ጨረታው ጋምቤላ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ነሐሴ 14/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው፡፡
- በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251911278481 ወይም +251910464495 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for disposal sale of assorted items (ferrous metals, ceramics, tires, vehicle spare parts, water, shower, and toilet fixtures) as-is. Bidders must purchase tender documents and provide a 2% bid security via CPO or bank guarantee.
