የህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት እድሳትና ጥገና ሥራዎች (ሎቶች 1-11)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስር የሚገኘው ህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት
- ሎት 1 የተማሪዎች ሪከርድ ክፍልና የማእከል እድሳት
- ሎት 2. የቅድመ አንደኛ አስተባባሪ ቢሮ እድሳት
- ሎት 3. የኬጂ እና የአንደኛ ደረጃ የተማሪዎች መጸዳጃ ቤት ጥገና
- ሎት 4. የቴራዞ ንጣፍ, የልዩ ፍላጎት መሸጋገሪያ ራምፕ
- ሎት 5. ላተራል፤ ሼልፍ፡የጠረጴዛ መሳቢያ፣ የበር መስኮትና የተማሪዎች ዴስክ ጥገና
- ሎት 6. መጸዳጃ ቤት ማስመጠጥ
- ሎት 7. ከለር ፕሪንተር ጥገናና ኮምፒዩተር ከፕሪንተር ጋር በኔትወርክ ማገናኘት፣ አንቲ ቫይረስ ኮምፒውተር ላይ መጫን፣ የኮፒ ማሽን ጥገናና ማባዣ ማሽን ጥገና
- ሎት 8. ከአንድ ማእከል የሬዲዮ ስርጭት ዝርጋታ፣ የተማሪ ክፍሎች መብራት ጥገናና ሬክላም ከነላይት ቦክሱ
- ሎት 9. ላተራል፤ ሼልፍ፡የጠረጴዛ መሳቢያ የበር፣ መስኮትና የተማሪዎች ዴስክ ጥገና
- ሎት 1ዐ. የመማሪያ ክፍል ቀለም እድሳት
- ሎት 11. የመምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች መዝናኛ ክበብ አገልግሎት
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የሰነድ ማስረጃዎችን ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው።
- ለመምህራንና ለአስተዳደር ሠራተኞች ክበብ ወንበሮች፤ ጠረጴዛዎች፤ የሻይ ማሽን፤ እስቶቭ፤ የምግብ ሳህንና ትሪ፤ የእጅ ማስታጠቢያ እንስራ የመሳሰሉትን ት/ቤቱ ያቀርባል በተጨማሪም የውሃና የመብራት አገልግሎትንና የቤት ኪራይ ት/ቤቱ ይሸፍናል።
- ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ካራ ቆሬ ከሚገኘው የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ስር የሚገኘው የህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው ሰነዱን ከፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በት/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በመቅረብ ጠዋት ከ2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ሰነድ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጥቃቅንና አነስተኛ የሆናችሁ ተወዳዳሪዎች የምታመጡት ደብዳቤ በጽ/ቤት ኃላፊ ብቻ የተፈረመ መሆን አለበት።
- ት/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከቫት ጋር መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1.ብር 3000፤ ለሎት 2 ብር 3000፤ ለሎት 3 ብር 2000፤ ለሎት 4 ብር 2000፤ ለሎት 5 ብር 2000፤ ለሎት 6 ብር 2000፤ ሎት 7 ብር 3000፤ ሎት 8 ብር 2000፤ ሎት 9 ብር 2000፤ ሎት 10 ብር 2000፤ ሎት 11 ብር 2000 የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ cpo ቼክ በት/ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባችኋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ሥራ ሲጨርሱ ሥራውን ለሚያዩ ክፍሎች ማስረከብ ይኖርባችዋል።
አድራሻ፡- በኮልፌ ቀ/ክ/ከ ወረዳ 02 ህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት ልዩ ቦታው ካራ ቆሬ ከቢቂላ መናፈሻ ጀርባ / ከኮንዶሚኒየም አጠገብ
ስልክ፡- 011 369 4712 / 09 12 12 03 94
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ህዳሴ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Renovation and maintenance works at Hidase Primary School across 11 lots, including classroom repairs, plumbing, painting, IT and printer maintenance, and staff club furnishing. Bidders must hold a valid trade license, pay current taxes, and be VAT registered.
