ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ በአዲስ አበባ ከተማ’ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ዋና መ/ቤት ሕንፃ ላይ ለሚገኙ ሠራተኞቹ ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት የሥራ ቀናት የምሳ አገልግሎት ማቅረብ የሚችል ድርጅት ወይም ግለሰብ በጨረታ በማወዳደር አሸናፊ ከሆነው ጋር ውል በመፈፀም አገልግሎቱን ለመስጠት ይፈልጋል፡፡
በድጋሜ የወጣ የሠራተኞች የምሳ አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ በአዲስ አበባ ከተማ’ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ዋና መ/ቤት ሕንፃ ላይ ለሚገኙ ሠራተኞቹ ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት የሥራ ቀናት የምሳ አገልግሎት ማቅረብ የሚችል ድርጅት ወይም ግለሰብ በጨረታ በማወዳደር አሸናፊ ከሆነው ጋር ውል በመፈፀም አገልግሎቱን ለመስጠት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የታደሰ ንግድ ፍቃድ’ ቲን ሰርተፍኬት’ የሙያ ፍቃድ እንዲሁም አገልግሎቱን የማቅረብ ልምድ ያላቸውን ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች ስለ ምሳ አገልግሎቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ከነሀሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በሥራ ሰዓት ቴዎድሮስ አደባባይ አከባቢ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው ገንዘብ ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲ.ፒ.ኦ.) በሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ ስም በማዘጋጀት ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሥራው የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች ለማሟላት በሕግ ፊት ዉል መፈፀም የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተሟላ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ከዋጋ ማቅረቢያ እና ደጋፊ የሥራ ልምድ ማስረጃዎች ጋር በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እስከ ነሃሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት ሕንፃ 9ኛ ፎቅ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በዕለቱ ነሀሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ሕንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ኩባንያው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 1 26 34 34 የውስጥ መስመር 190/207 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
