ዘመናዊ የምድር ሚዛን እና CCTV ካሜራ ግዥ
ዘመናዊ የምድር ሚዛን እና CCTV ካሜራ ግዥ
ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት
ሎት 1፡- የጫት ቀረጥ ስራውን ለማከናወን ተሽከርካሪውን ከነጭነቱ የሚጭን ዘመናዊ የምድር ሚዛን
ሎት 2፡- ለጫት ቀረጥ ኬላ ላይ የሚገጠም CCTV ካሜራ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ ፡-
- ለስራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ለስራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ ግዥው ከ200000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያላቸው፤
- የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ ዋና የስራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘውትር በስራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮ. ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናዉን በታሸገ ኤንቨሎፕ በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ ስድስት /16/ቀን ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በቀን 23-12-208 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ላይ በግዥ⁄ ፋይ/ንብ/ አስ ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻ ቀን መንግስት ዝግ የሚደርጋቸው በዓላት ፣ ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ
- ሎት 1፡- 50000(ሀምሳ ሺህ ብር)
- ሎት 2፡- 20000(ሀያ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ትዕዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10 % ማስያዝ ይኖርበታል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ፤ በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 033 554 0144 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
ከሚሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Procurement of a modern vehicle-mounted weighbridge and CCTV cameras for khat tax operations in Kemise town, via national open tender. Bidders need valid licenses, tax clearance, registration, and TIN/VAT if applicable.
